ኢሳይያስ 12:1-6

  • የምስጋና መዝሙር (1-6)

    • ‘ያህ ይሖዋ ብርታቴ ነው’ (2)

12  በዚያ ቀን በእርግጥ እንዲህ ትላለህ፦ “ይሖዋ ሆይ፣ ተቆጥተኸኝ የነበረ ቢሆንምቁጣህ ቀስ በቀስ ስለበረደደግሞም ስላጽናናኸኝ አመሰግንሃለሁ።+   እነሆ፣ አምላክ አዳኜ ነው!+ በእሱ እታመናለሁ፤ ምንም የሚያስፈራኝ ነገር የለም፤+ያህ* ይሖዋ ብርታቴና ኃይሌ ነው፤ለእኔም አዳኝ ሆኖልኛል።”+   ከመዳን ምንጮችበደስታ ውኃ ትቀዳላችሁ።+   በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፦ “ይሖዋን አመስግኑ! ስሙን ጥሩ፤ሥራውን በሕዝቦች መካከል አስታውቁ!+ ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱን አውጁ።+   አስደናቂ ነገሮችን+ ስላከናወነ ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ።+ ይህም በመላው ምድር ይታወጅ።   እናንተ የጽዮን ነዋሪዎች* ሆይ፣ ጩኹ፤ በደስታም እልል በሉ፤የእስራኤል ቅዱስ በመካከላችሁ ታላቅ ነውና።”

የግርጌ ማስታወሻዎች

“ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።
ቃል በቃል “አንቺ የጽዮን ነዋሪ።” ሕዝቡ በጥቅሉ በአንስታይ ፆታ መጠራቱን ያሳያል።