አሞጽ 9:1-15
9 ይሖዋን ከመሠዊያው በላይ ቆሞ አየሁት፤+ እሱም እንዲህ አለ፦ “የዓምዱን አናት ምታ፤ መሠረቶቹም ይናወጣሉ። አናታቸውን ቁረጥ፤ የቀሩትንም በሰይፍ እገድላቸዋለሁ። የሚሸሽ ሁሉ አያመልጥም፤ ለማምለጥ የሚሞክርም ሁሉ አይሳካለትም።+
2 በመቃብር* ለመደበቅ ወደ ታች ቢቆፍሩምእጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች፤ወደ ሰማያት ቢወጡምከዚያ አወርዳቸዋለሁ።
3 ቀርሜሎስ አናት ላይ ቢደበቁምፈልጌ ከዚያ አወጣቸዋለሁ።+
ወደ ታችኛው የባሕር ወለል ወርደው ራሳቸውን ከዓይኔ ቢሰውሩምበዚያ እባቡ እንዲነድፋቸው አዘዋለሁ።
4 ጠላቶቻቸው ማርከው ቢወስዷቸውበዚያ ሰይፍ አዛለሁ፤ ሰይፉም ይገድላቸዋል፤+ለመልካም ሳይሆን ለክፉ ዓይኔን በእነሱ ላይ አደርጋለሁ።+
5 ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ፣ አገሪቱን* ይነካልና፤እሷም ትቀልጣለች፤+ በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ለሐዘን ይዳረጋሉ፤+ምድሪቱ በሙሉ እንደ አባይ ወደ ላይ ትነሳለች፤በግብፅ እንዳለውም የአባይ ወንዝ ተመልሳ ወደ ታች ትወርዳለች።+
6 ‘ደረጃዎቹን በሰማያት የሚሠራው፣ከምድርም በላይ ሕንፃውን* የሚገነባው፣ወደ ምድር ያፈሰው ዘንድየባሕርን ውኃ ወደ እሱ የሚጠራው፣+ስሙ ይሖዋ ነው።’+
7 ‘የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች* አይደላችሁም?’ ይላል ይሖዋ።
‘እስራኤልን ከግብፅ ምድር፣+ ፍልስጤማውያንን ከቀርጤስ፣+ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁም?’+
8 ‘እነሆ፣ የሉዓላዊው ጌታ የይሖዋ ዓይኖች በኃጢአተኛው መንግሥት ላይ ናቸው፤እሱም ከምድር ገጽ ያጠፋዋል።+
ይሁንና የያዕቆብን ቤት ሙሉ በሙሉ አልደመስስም’+ ይላል ይሖዋ።
9 ‘እነሆ፣ እኔ ትእዛዝ እሰጣለሁና፤ሰው እህልን በወንፊት እንደሚነፋናአንዲትም ጠጠር ወደ ምድር እንደማትወድቅ ሁሉየእስራኤልንም ቤት በብሔራት ሁሉ መካከል እነፋለሁ።+
10 “ጥፋት አይደርስብንም ወይም ወደ እኛ አይጠጋም” የሚሉበሕዝቤ መካከል ያሉ ኃጢአተኞች ሁሉ በሰይፍ ይሞታሉ።’
11 ‘በዚያ ቀን የፈረሰውን የዳዊትን ዳስ አቆማለሁ፤+በግንቡ ላይ ያሉትን ክፍተቶች እጠግናለሁ፤*ፍርስራሾቹንም አድሳለሁ፤በጥንት ዘመን እንደነበረው ዳግም እገነባዋለሁ፤+
12 በመሆኑም ከኤዶምና ስሜ ከተጠራባቸው ብሔራት ሁሉ የቀረውን ይወርሳሉ’+ይላል ይህን የሚያደርገው ይሖዋ።
13 ‘እነሆ፣ እንዲህ የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ፤‘አራሹ አጫጁ ላይ ይደርስበታል፤ዘሪውም ወይን ጨማቂው ላይ ይደርስበታል፤+ተራሮችም ጣፋጭ የወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፤+ኮረብቶችም ሁሉ በወይን ጠጅ ይጥለቀለቃሉ።*+
14 ከሕዝቤ ከእስራኤል የተማረኩትን ሰዎች መልሼ እሰበስባለሁ፤+እነሱም የወደሙትን ከተሞች መልሰው በመገንባት ይኖሩባቸዋል፤+የወይን ተክል ተክለው የወይን ጠጁን ይጠጣሉ፤+አትክልት ተክለው ፍሬውን ይበላሉ።’+
15 ‘በምድራቸው ላይ እተክላቸዋለሁ፤ከሰጠኋቸውም ምድር ላይዳግመኛ አይነቀሉም’+ ይላል አምላክህ ይሖዋ።”

