ናሆም 3:1-19

  • “ለደም አፍሳሿ ከተማ ወዮላት!” (1-19)

    • በነነዌ ላይ ለተላለፈው ፍርድ ምክንያት የሆኑ ነገሮች (1-7)

    • ነነዌ እንደ ኖአሞን ትወድቃለች (8-12)

    • ነነዌ መጥፋቷ የማይቀር ነው (13-19)

3  ለደም አፍሳሿ ከተማ ወዮላት! በማታለልና በዝርፊያ የተሞላች ናት። ከማደን ቦዝና አታውቅም!   የአለንጋ ድምፅና የመንኮራኩር* ኳኳቴ ይሰማል፤ፈረሶች ሲጋልቡና ሠረገሎች ሲፈተለኩ ይታያል።   ፈረስ ጋላቢው ይጋልባል፤ ሰይፉ ያንጸባርቃል፤ ጦሩ ያብረቀርቃል፤የተገደሉት በጣም ብዙ ናቸው፤ የአስከሬን ክምር ይታያል፤ሬሳው ስፍር ቁጥር የለውም። አስከሬኖቹም ያደናቅፏቸዋል።   ይህ የሆነው ዝሙት አዳሪዋ በምትፈጽመው በርካታ የአመንዝራነት ተግባር የተነሳ ነው፤እሷ ብሔራትን በምንዝሯ፣ ወገኖችንም በጥንቆላዋ የምታጠምድ፣የምታምርና የምትማርክ እንዲሁም በጥንቆላ የተካነች ናት።   “እነሆ፣ በአንቺ* ላይ ተነስቻለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤+“ቀሚስሽን እስከ ፊትሽ ድረስ እገልበዋለሁ፤ብሔራትም እርቃንሽን፣መንግሥታትም ነውርሽን እንዲያዩ አደርጋለሁ።   ቆሻሻ እደፋብሻለሁ፤የተናቅሽ አደርግሻለሁ፤ማላገጫም እንድትሆኚ አደርጋለሁ።+   አንቺን የሚያይ ሁሉ ከአንቺ ይሸሻል፤+ደግሞም ‘ነነዌ ወድማለች! የሚያዝንላት ማን ነው?’ ይላል። አንቺን የሚያጽናና ከየት ማግኘት እችላለሁ?   አንቺ በአባይ የመስኖ ቦዮች+ አጠገብ ከነበረችው ከኖአሞን*+ ትሻያለሽ? እሷ በውኃ የተከበበች ነበረች፤ባሕሩም ሀብት ያስገኝላት፣ እንደ ቅጥርም ሆኖ ያገለግላት ነበር።   ኢትዮጵያና ግብፅ ገደብ የለሽ የኃይል ምንጮቿ ነበሩ። ፑጥና+ ሊቢያውያን ረዳቶቿ ነበሩ።+ 10  ይሁንና እሷም እንኳ በግዞት ተወሰደች፤ተማርካም ሄደች።+ ልጆቿም በየመንገዱ ማዕዘን* ተፈጠፈጡ። በተከበሩ ሰዎቿ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፤ታላላቅ ሰዎቿም ሁሉ በእግር ብረት ታሰሩ። 11  አንቺም ትሰክሪያለሽ፤+ደግሞም ትሰወሪያለሽ። ከጠላት የምትሸሸጊበት ቦታ ትፈልጊያለሽ። 12  ምሽጎችሽ ሁሉ የመጀመሪያዎቹን የበሰሉ ፍሬዎች እንደያዙ የበለስ ዛፎች ናቸው፤ዛፎቹ ከተነቀነቁ ፍሬዎቹ ረግፈው በበላተኛ አፍ ውስጥ ይወድቃሉ። 13  እነሆ፣ ወታደሮችሽ በመካከልሽ እንዳሉ ሴቶች ናቸው። የምድርሽ በሮች ለጠላቶችሽ ወለል ብለው ይከፈታሉ። የበሮችሽን መቀርቀሪያዎች እሳት ይበላቸዋል። 14  ለከበባው ውኃ ቅጂ!+ ምሽጎችሽን አጠናክሪ። ማጥ ውስጥ ግቢ፤ ጭቃውንም ርገጪ፤የጡብ ቅርጽ ማውጫውንም ያዢ። 15  ይህም ሆኖ እሳት ይበላሻል። ሰይፍ ይቆርጥሻል።+ እንደ ኩብኩባ ይበላሻል።+ እንደ ኩብኩባ ተባዢ! አዎ፣ እንደ አንበጣ ተራቢ! 16  ነጋዴዎችሽን ከሰማያት ከዋክብት ይበልጥ አብዝተሻል። ኩብኩባው ቅርፊቱን ከላዩ ላይ ጥሎ ይበርራል። 17  ጠባቂዎችሽ እንደ አንበጣ፣መኮንኖችሽም እንደ አንበጣ መንጋ ናቸው። ቅዝቃዜ ባለበት ቀን በድንጋይ ቅጥሮች ውስጥ ይሰፍራሉ፤ፀሐይ ስትወጣ ግን በርረው ይሄዳሉ፤የት እንደደረሱም ማንም አያውቅም። 18  የአሦር ንጉሥ ሆይ፣ እረኞችህ እንቅልፍ ተጫጭኗቸዋል፤ታላላቅ ሰዎችህ በመኖሪያቸው ይቀመጣሉ። ሕዝብህ በተራሮቹ ላይ ተበታትነዋል፤የሚሰበስባቸውም የለም።+ 19  የደረሰብህን መቅሰፍት የሚያቆም ነገር የለም። ቁስልህ ሊድን የሚችል አይደለም። ስለ አንተ ወሬ የሚሰሙ ሁሉ ያጨበጭባሉ፤+በማያባራው ጭካኔህ ያልተጎዳ ማን አለና?”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ተሽከርካሪ እግር።
ነነዌን ያመለክታል።
ቴብስን ያመለክታል።
ቃል በቃል “በጎዳናዎች ሁሉ ራስ ላይ።”