ነህምያ 7:1-73

  • የከተማዋ መዝጊያዎችና በር ጠባቂዎቹ (1-4)

  • ከግዞት የተመለሱት ሰዎች ዝርዝር (5-69)

    • የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች (46-56)

    • የሰለሞን አገልጋዮች ወንዶች ልጆች (57-60)

  • ለሥራው የተደረገ መዋጮ (70-73)

7  እኔም ቅጥሩ እንደገና ተገንብቶ እንዳለቀ+ መዝጊያዎቹን+ ገጠምኩ፤ ከዚያም በር ጠባቂዎቹ፣+ ዘማሪዎቹና+ ሌዋውያኑ+ ተሾሙ።  በኋላም ወንድሜን ሃናኒን፣+ የምሽጉ+ አለቃ ከሆነው ከሃናንያህ ጋር በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኩት፤ ምክንያቱም ሃናንያህ እምነት የሚጣልበትና ከሌሎቹ ሁሉ ይበልጥ እውነተኛውን አምላክ የሚፈራ ሰው ነበር።+  እንዲህም አልኳቸው፦ “የኢየሩሳሌም በሮች ፀሐይ ሞቅ እስከሚል ድረስ መከፈት የለባቸውም፤ ጠባቂዎቹ በጥበቃ ሥራቸው ላይ እያሉ በሮቹን መዝጋትና መቀርቀር ይኖርባቸዋል። እንዲሁም የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች ጠባቂዎች አድርጋችሁ መድቡ፤ የተወሰኑት ሰዎች በተመደቡበት የጥበቃ ቦታ፣ ሌሎቹ ደግሞ ከቤታቸው ፊት ለፊት ይጠብቁ።”  ከተማዋ ሰፊና ትልቅ ነበረች፤ በውስጧ የነበሩት ሰዎች ጥቂት ሲሆኑ+ ቤቶቹም እንደገና አልተገነቡም ነበር።  ሆኖም አምላኬ የተከበሩትን ሰዎች፣ የበታች ገዢዎቹንና ሕዝቡን በአንድነት እንድሰበስብና በየዘር ሐረጋቸው እንዲመዘገቡ+ እንዳደርግ ይህን ሐሳብ በልቤ ውስጥ አኖረ። ከዚያም መጀመሪያ ላይ የመጡትን ሰዎች የዘር ሐረግ ዝርዝር የያዘ መጽሐፍ አገኘሁ፤ በውስጡም ተጽፎ ያገኘሁት ይህ ነው፦  የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር+ በግዞት ወስዷቸው+ የነበሩትና ከምርኮ ነፃ ወጥተው፣ በኋላ ላይ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ይኸውም ወደየከተሞቻቸው የተመለሱት የአውራጃው ነዋሪዎች እነዚህ ናቸው፤+  ከዘሩባቤል፣+ ከየሆሹዋ፣+ ከነህምያ፣ ከአዛርያስ፣ ከራሚያህ፣ ከናሃማኒ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከቢልሻን፣ ከሚስጴሬት፣ ከቢግዋይ፣ ከነሁም እና ከባአናህ ጋር የመጡት እነዚህ ናቸው። የእስራኤላውያን ወንዶች ቁጥር የሚከተሉትን ይጨምራል፦+  የፓሮሽ ወንዶች ልጆች 2,172፣  የሰፋጥያህ ወንዶች ልጆች 372፣ 10  የኤራ+ ወንዶች ልጆች 652፣ 11  የየሹዋና የኢዮዓብ+ ወንዶች ልጆች የሆኑት የፓሃትሞአብ+ ወንዶች ልጆች 2,818፣ 12  የኤላም+ ወንዶች ልጆች 1,254፣ 13  የዛቱ ወንዶች ልጆች 845፣ 14  የዛካይ ወንዶች ልጆች 760፣ 15  የቢኑይ ወንዶች ልጆች 648፣ 16  የቤባይ ወንዶች ልጆች 628፣ 17  የአዝጋድ ወንዶች ልጆች 2,322፣ 18  የአዶኒቃም ወንዶች ልጆች 667፣ 19  የቢግዋይ ወንዶች ልጆች 2,067፣ 20  የአዲን ወንዶች ልጆች 655፣ 21  የሕዝቅያስ ልጅ የአጤር ወንዶች ልጆች 98፣ 22  የሃሹም ወንዶች ልጆች 328፣ 23  የቤጻይ ወንዶች ልጆች 324፣ 24  የሃሪፍ ወንዶች ልጆች 112፣ 25  የገባኦን+ ወንዶች ልጆች 95፣ 26  የቤተልሔምና የነጦፋ ሰዎች 188፣ 27  የአናቶት+ ሰዎች 128፣ 28  የቤትአዝማዌት ሰዎች 42፣ 29  የቂርያትየአሪም፣+ የከፊራና የበኤሮት+ ሰዎች 743፣ 30  የራማና የጌባ+ ሰዎች 621፣ 31  የሚክማስ+ ሰዎች 122፣ 32  የቤቴልና+ የጋይ+ ሰዎች 123፣ 33  የሌላኛው ነቦ ሰዎች 52፣ 34  የሌላኛው ኤላም ወንዶች ልጆች 1,254፣ 35  የሃሪም ወንዶች ልጆች 320፣ 36  የኢያሪኮ ወንዶች ልጆች 345፣ 37  የሎድ፣ የሃዲድና የኦኖ+ ወንዶች ልጆች 721፣ 38  የሰናአ ወንዶች ልጆች 3,930። 39  ካህናቱ+ የሚከተሉት ናቸው፦ ከየሹዋ ወገን የሆነው የየዳያህ ወንዶች ልጆች 973፣ 40  የኢሜር ወንዶች ልጆች 1,052፣ 41  የጳስኮር+ ወንዶች ልጆች 1,247፣ 42  የሃሪም+ ወንዶች ልጆች 1,017። 43  ሌዋውያኑ+ የሚከተሉት ናቸው፦ የሆዳውያህ ወንዶች ልጆች የሆኑት የየሹዋና የቃድሚኤል+ ወንዶች ልጆች 74። 44  ዘማሪዎቹ+ የአሳፍ+ ወንዶች ልጆች 148። 45  በር ጠባቂዎቹ+ የሻሉም ወንዶች ልጆች፣ የአጤር ወንዶች ልጆች፣ የታልሞን ወንዶች ልጆች፣ የአቁብ+ ወንዶች ልጆች፣ የሃጢጣ ወንዶች ልጆችና የሾባይ ወንዶች ልጆች 138። 46  የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች*+ የሚከተሉት ናቸው፦ የጺሃ ወንዶች ልጆች፣ የሃሱፋ ወንዶች ልጆች፣ የታባኦት ወንዶች ልጆች፣ 47  የቀሮስ ወንዶች ልጆች፣ የሲአ ወንዶች ልጆች፣ የፓዶን ወንዶች ልጆች፣ 48  የለባና ወንዶች ልጆች፣ የሃጋባ ወንዶች ልጆች፣ የሳልማይ ወንዶች ልጆች፣ 49  የሃናን ወንዶች ልጆች፣ የጊዴል ወንዶች ልጆች፣ የጋሃር ወንዶች ልጆች፣ 50  የረአያህ ወንዶች ልጆች፣ የረጺን ወንዶች ልጆች፣ የነቆዳ ወንዶች ልጆች፣ 51  የጋዛም ወንዶች ልጆች፣ የዑዛ ወንዶች ልጆች፣ የፓሰአህ ወንዶች ልጆች፣ 52  የቤሳይ ወንዶች ልጆች፣ የመኡኒም ወንዶች ልጆች፣ የነፉሸሲም ወንዶች ልጆች፣ 53   የባቅቡቅ ወንዶች ልጆች፣ የሃቁፋ ወንዶች ልጆች፣ የሃርሑር ወንዶች ልጆች፣ 54  የባጽሊት ወንዶች ልጆች፣ የመሂዳ ወንዶች ልጆች፣ የሃርሻ ወንዶች ልጆች፣ 55  የባርቆስ ወንዶች ልጆች፣ የሲሳራ ወንዶች ልጆች፣ የተማ ወንዶች ልጆች፣ 56  የነጺሃ ወንዶች ልጆችና የሃጢፋ ወንዶች ልጆች። 57   የሰለሞን አገልጋዮች+ ወንዶች ልጆች የሚከተሉት ናቸው፦ የሶጣይ ወንዶች ልጆች፣ የሶፈረት ወንዶች ልጆች፣ የፐሪዳ ወንዶች ልጆች፣ 58  የያአላ ወንዶች ልጆች፣ የዳርቆን ወንዶች ልጆች፣ የጊዴል ወንዶች ልጆች፣ 59  የሰፋጥያህ ወንዶች ልጆች፣ የሃጢል ወንዶች ልጆች፣ የፖክሄሬትሃጸባይም ወንዶች ልጆችና የአምዖን ወንዶች ልጆች። 60  የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና*+ የሰለሞን አገልጋዮች ወንዶች ልጆች በአጠቃላይ 392 ነበሩ። 61  ከቴልመላ፣ ከቴልሃርሻ፣ ከከሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር የወጡት ሆኖም ከየትኛው የአባቶች ቤትና የዘር ሐረግ እንደመጡ በውል መለየትም ሆነ እስራኤላዊ መሆን አለመሆናቸውን በትክክል ማረጋገጥ ያልቻሉት የሚከተሉት ናቸው፦+ 62  የደላያህ ወንዶች ልጆች፣ የጦብያ ወንዶች ልጆችና የነቆዳ ወንዶች ልጆች 642። 63  ከካህናቱም መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦ የሃባያ ወንዶች ልጆች፣ የሃቆጽ+ ወንዶች ልጆች እንዲሁም ከጊልያዳዊው ከቤርዜሊ ሴቶች ልጆች መካከል አንዷን ያገባውና በስማቸው የተጠራው የቤርዜሊ+ ወንዶች ልጆች። 64  እነዚህ የዘር ሐረጋቸውን ለማረጋገጥ በመዝገቡ ላይ የቤተሰባቸውን ስም ለማግኘት ቢጥሩም ሊገኙ አልቻሉም፤ በመሆኑም ከክህነት አገልግሎቱ ታገዱ።*+ 65  ገዢውም*+ በኡሪምና በቱሚም+ አማካኝነት ምክር የሚጠይቅ ካህን እስኪገኝ ድረስ እጅግ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች መብላት እንደማይኖርባቸው ነገራቸው።+ 66  መላው ጉባኤ በአጠቃላይ 42,360 ነበር፤+ 67  ይህ 7,337 ወንድና ሴት ባሪያዎቻቸውን አይጨምርም፤+ በተጨማሪም 245 ወንድና ሴት ዘማሪዎች+ ነበሯቸው። 68  ከዚህም ሌላ 736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች 69  እንዲሁም 435 ግመሎችና 6,720 አህዮች ነበሯቸው። 70  ከአባቶች ቤት መሪዎች መካከል ለሥራው መዋጮ ያደረጉ ነበሩ።+ ገዢው* 1,000 የወርቅ ድራክማ፣* 50 ጎድጓዳ ሳህኖችና 530 የካህናት ቀሚሶች ለግምጃ ቤቱ ሰጠ።+ 71  ከአባቶች ቤት መሪዎች መካከል አንዳንዶቹ ለሥራው ማስኬጃ የሚሆን 20,000 የወርቅ ድራክማና 2,200 የብር ምናን* ለግምጃ ቤቱ ሰጡ። 72  የቀረው ሕዝብ ደግሞ 20,000 የወርቅ ድራክማ፣ 2,000 የብር ምናን እና 67 የካህናት ቀሚሶች ሰጠ። 73  ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ ዘማሪዎቹ፣+ ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶቹ፣ የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹና* የቀሩት እስራኤላውያን በሙሉ በየከተሞቻቸው ሰፈሩ።+ በሰባተኛውም ወር+ እስራኤላውያን በየከተሞቻቸው ይኖሩ ነበር።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ናታኒሞቹ።” ቃል በቃል “የተሰጡት ሰዎች።”
ወይም “የናታኒሞቹና።” ቃል በቃል “የተሰጡት ሰዎችና።”
ወይም “እንደረከሱ ተቆጥረው ከክህነት አገልግሎቱ ተገለሉ።”
ወይም “ቲርሻታውም።” ለአንድ የአውራጃ ገዢ የሚሰጥ የፋርሳውያን የማዕረግ ስም ነው።
ወይም “ቲርሻታው።” ለአንድ የአውራጃ ገዢ የሚሰጥ የፋርሳውያን የማዕረግ ስም ነው።
አብዛኛውን ጊዜ 8.4 ግራም ከሚመዝነው የፋርሳውያን የወርቅ ዳሪክ ጋር እኩል መጠን አለው። በግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ላይ ከተጠቀሰው ድራክማ የተለየ ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
በዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ አንድ ምናን 570 ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ናታኒሞቹና።” ቃል በቃል “የተሰጡት ሰዎችና።”