ነህምያ 11:1-36

  • እስራኤላውያን ዳግመኛ በኢየሩሳሌም መኖር ጀመሩ (1-36)

11  በዚህ ጊዜ የሕዝቡ መኳንንት የሚኖሩት በኢየሩሳሌም ነበር፤+ የቀሩት ሰዎች ግን ከአሥር ሰው አንዱ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም እንዲኖርና የቀሩት ዘጠኙ ደግሞ በሌሎች ከተሞች እንዲኖሩ ዕጣ+ ጣሉ።  በተጨማሪም ሕዝቡ በኢየሩሳሌም ለመኖር ፈቃደኛ የሆኑትን ሰዎች በሙሉ ባረኳቸው።  በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩት የአውራጃው መሪዎች እነዚህ ናቸው። (የቀሩት እስራኤላውያን፣ ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹና*+ የሰለሞን አገልጋዮች+ ወንዶች ልጆች በሌሎቹ የይሁዳ ከተሞች ማለትም እያንዳንዳቸው በየከተሞቻቸው ባለው በየራሳቸው ርስት ይኖሩ ነበር።+  በተጨማሪም ከይሁዳና ከቢንያም ሰዎች መካከል የተወሰኑት በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር።) ከይሁዳ ሰዎች መካከል ከፋሬስ+ ቤተሰብ የሆነው የመላልኤል ልጅ፣ የሰፋጥያህ ልጅ፣ የአማርያህ ልጅ፣ የዘካርያስ ልጅ፣ የዖዝያ ልጅ አታያህ  እንዲሁም ከሴሎማውያን ቤተሰብ የሆነው የዘካርያስ ልጅ፣ የዮያሪብ ልጅ፣ የአዳያህ ልጅ፣ የሃዛያህ ልጅ፣ የኮልሆዜ ልጅ፣ የባሮክ ልጅ ማአሴያህ ነበሩ።  በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩት የፋሬስ ወንዶች ልጆች በአጠቃላይ 468 ብቃት ያላቸው ወንዶች ነበሩ።  የቢንያም ሰዎች የሚከተሉት ነበሩ፦ የየሻያህ ልጅ፣ የኢቲኤል ልጅ፣ የማአሴያህ ልጅ፣ የቆላያህ ልጅ፣ የፐዳያህ ልጅ፣ የዮኤድ ልጅ፣ የመሹላም ልጅ ሳሉ፣+  ከእሱ ቀጥሎ ደግሞ ጋባይ እና ሳላይ ሲሆኑ በአጠቃላይ 928 ነበሩ፤  የዚክሪ ልጅ ኢዩኤል የእነሱ የበላይ ተመልካች ነበር፤ የሃስኑአ ልጅ ይሁዳ ደግሞ በከተማዋ ላይ ሁለተኛ አዛዥ ነበር። 10  ከካህናቱ መካከል ደግሞ የሚከተሉት ነበሩ፦ የዮያሪብ ልጅ የዳያህ፣ ያኪን፣+ 11  የእውነተኛው አምላክ ቤት* መሪ የሆነው የአኪጡብ+ ልጅ፣ የመራዮት ልጅ፣ የሳዶቅ ልጅ፣ የመሹላም ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ ሰራያህ፤ 12  እንዲሁም የቤቱን ሥራ የሠሩት ወንድሞቻቸው 822፤ የማልኪያህ ልጅ፣ የጳስኮር+ ልጅ፣ የዘካርያስ ልጅ፣ የአማሲ ልጅ፣ የፐላልያህ ልጅ፣ የየሮሃም ልጅ አዳያህ፣ 13  የአባቶች ቤት መሪዎች የሆኑት ወንድሞቹ 242፤ እንዲሁም የኢሜር ልጅ፣ የመሺሌሞት ልጅ፣ የአህዛይ ልጅ፣ የአዛርዔል ልጅ አማሽሳይ 14  እንዲሁም ኃያላንና ጀግኖች የሆኑት ወንድሞቻቸው 128፤ የእነሱ የበላይ ተመልካች የአንድ ታዋቂ ቤተሰብ አባል የሆነው ዛብድኤል ነበር። 15  ከሌዋውያኑ መካከል ደግሞ የሚከተሉት ነበሩ፦ የቡኒ ልጅ፣ የሃሻብያህ ልጅ፣ የአዝሪቃም ልጅ፣ የሃሹብ ልጅ ሸማያህ፣+ 16  ከእውነተኛው አምላክ ቤት ጋር በተያያዘ በውጭ ያሉትን ጉዳዮች በበላይነት ከሚከታተሉት የሌዋውያን መሪዎች መካከል ሻበታይ+ እና ዮዛባድ፤+ 17  የውዳሴ መዝሙሩንና በጸሎት ጊዜ+ የሚቀርበውን ውዳሴ የሚመራው የአሳፍ+ ልጅ፣ የዛብዲ ልጅ፣ የሚክያስ ልጅ ማታንያህ፣+ ከወንድሞቹ ሁለተኛ የሆነው ባቅቡቅያ እንዲሁም የየዱቱን+ ልጅ፣ የጋላል ልጅ፣ የሻሙአ ልጅ አብዳ። 18  በቅድስቲቱ ከተማ የነበሩት ሌዋውያን በአጠቃላይ 284 ነበሩ። 19  በር ጠባቂዎቹ አቁብ፣ ታልሞን+ እና በየበሮቹ ላይ የሚጠብቁት ወንድሞቻቸው ደግሞ 172 ነበሩ። 20  ከእስራኤላውያን፣ ከካህናቱና ከሌዋውያኑ የቀሩት ደግሞ በሌሎቹ የይሁዳ ከተሞች ሁሉ እያንዳንዳቸው በውርስ ባገኙት ርስት ላይ ይኖሩ ነበር። 21  የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች*+ በኦፌል+ ይኖሩ የነበረ ሲሆን ጺሃ እና ጊሽፓ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች* ኃላፊዎች ነበሩ። 22  በኢየሩሳሌም የነበሩት ሌዋውያን የበላይ ተመልካች ከዘማሪዎቹ ከአሳፍ ልጆች መካከል የሚካ ልጅ፣ የማታንያህ+ ልጅ፣ የሃሻብያህ ልጅ፣ የባኒ ልጅ ዑዚ ነበር፤ እሱም በእውነተኛው አምላክ ቤት ሥራ ላይ ኃላፊ ነበር። 23  እነሱን በተመለከተ የወጣ ንጉሣዊ ትእዛዝ ነበር፤+ ለዘማሪዎቹ በየዕለቱ የሚያስፈልገውን ነገር በማቅረብ ረገድም ቋሚ የሆነ ዝግጅት ነበር። 24  የይሁዳ ልጅ ከሆነው ከዛራ ልጆች መካከል የመሺዛቤል ልጅ ፐታያህ ከሕዝቡ ጋር የተያያዘውን ማንኛውንም ጉዳይ በተመለከተ የንጉሡ አማካሪ* ነበር። 25  የሰፈራ መንደሮቹ ከነእርሻ ቦታዎቻቸው የሚከተሉት ናቸው፦ ከይሁዳ ወንዶች ልጆች መካከል የተወሰኑት በቂርያትአርባና+ በሥሯ* ባሉት ከተሞች፣ በዲቦንና በሥሯ ባሉት ከተሞች፣ በየቃብጸኤል+ እና በሥሯ ባሉት የሰፈራ መንደሮች፣ 26  በየሹዋ፣ በሞላዳ፣+ በቤትጳሌጥ፣+ 27  በሃጻርሹአል፣+ በቤርሳቤህና በሥሯ* ባሉት ከተሞች፣ 28  በጺቅላግ፣+ በመኮና እና በሥሯ* ባሉት ከተሞች፣ 29  በኤንሪሞን፣+ በጾራ፣+ በያርሙት፣ 30  በዛኖሃ፣+ በአዱላምና በሥሯ ባሉት የሰፈራ መንደሮች፣ በለኪሶና+ በእርሻ ቦታዎቿ እንዲሁም በአዜቃና+ በሥሯ* ባሉት ከተሞች ይኖሩ ነበር። እነሱም ከቤርሳቤህ እስከ ሂኖም ሸለቆ+ ባለው አካባቢ ሰፈሩ። 31  የቢንያም ሰዎች ደግሞ ከጌባ+ ጀምሮ በሚክማሽ፣ በጋያ፣ በቤቴል+ እና በሥሯ* ባሉት ከተሞች፣ 32  በአናቶት፣+ በኖብ፣+ በአናንያ፣ 33  በሃጾር፣ በራማ፣+ በጊታይም፣ 34  በሃዲድ፣ በጸቦይም፣ በነባላጥ፣ 35  በሎድ እና በኦኖ+ እንዲሁም በእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ሸለቆ ተቀመጡ። 36  በይሁዳ ከነበሩት ሌዋውያን መካከል የተወሰኑት ቡድኖች በቢንያም ተመደቡ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “የናታኒሞቹና።” ቃል በቃል “የተሰጡት ሰዎችና።”
ወይም “ቤተ መቅደስ።”
ወይም “ናታኒሞቹ።” ቃል በቃል “የተሰጡት ሰዎች።”
ወይም “የናታኒሞቹ።” ቃል በቃል “የተሰጡት ሰዎች።”
ቃል በቃል “በንጉሡ እጅ።”
ወይም “በዙሪያዋ።”
ወይም “በዙሪያዋ።”
ወይም “በዙሪያዋ።”
ወይም “በዙሪያዋ።”
ወይም “በዙሪያዋ።”