ሶፎንያስ 1:1-18

  • የይሖዋ የፍርድ ቀን ቀርቧል (1-18)

    • የይሖዋ ቀን በፍጥነት እየቀረበ ነው (14)

    • “ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም” (18)

1  በይሁዳ ንጉሥ በአምዖን+ ልጅ በኢዮስያስ+ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ፣ ወደ አማርያህ ልጅ፣ ወደ ጎዶልያስ ልጅ፣ ወደ ኩሺ ልጅ፣ ወደ ሶፎንያስ* የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦   “ማንኛውንም ነገር ሙሉ በሙሉ ከምድር ገጽ ጠራርጌ አጠፋለሁ” ይላል ይሖዋ።+   “ሰውንና እንስሳን ጠራርጌ አጠፋለሁ። የሰማይ ወፎችንና የባሕር ዓሣንእንዲሁም ማሰናከያዎቹንና*+ ክፉ ሰዎችን ጠራርጌ አጠፋለሁ፤+ደግሞም የሰውን ዘር ከምድር ገጽ አስወግዳለሁ” ይላል ይሖዋ።   “በይሁዳና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ላይእጄን እዘረጋለሁ፤የባአልን ቀሪዎች* ሁሉና የባዕድ አምላክ ካህናትን ስምከሌሎቹ ካህናት ጋር ከዚህ ስፍራ ፈጽሜ አስወግዳለሁ፤+   በቤት ጣሪያዎች ላይ ሆነው ለሰማያት ሠራዊት የሚሰግዱትን+እንዲሁም በአንድ በኩል ለይሖዋ እየሰገዱና ታማኝ እንደሚሆኑ ቃል እየገቡ+በሌላ በኩል ግን ለማልካም ታማኝ እንደሚሆኑ ቃል የሚገቡትን አጠፋለሁ፤+   ደግሞም ይሖዋን ከመከተል ወደኋላ የሚሉትን፣+ይሖዋን የማይፈልጉትን ወይም እሱን የማይጠይቁትን አጠፋለሁ።”+   በሉዓላዊው ጌታ በይሖዋ ፊት ዝም በሉ፤ የይሖዋ ቀን ቀርቧልና።+ ይሖዋ መሥዋዕት አዘጋጅቷል፤ የጠራቸውን ቀድሷል።   “በይሖዋ የመሥዋዕት ቀን መኳንንቱን፣የንጉሡን ወንዶች ልጆችና+ የባዕዳንን ልብስ የሚለብሱትን ሁሉ እቀጣለሁ።   በዚያም ቀን መድረኩ* ላይ የሚወጡትን ሁሉ፣የጌቶቻቸውንም ቤት በዓመፅና በማታለል የሚሞሉትን እቀጣለሁ። 10  በዚያም ቀን” ይላል ይሖዋ፣“ከዓሣ በር+ የጩኸት ድምፅ፣ከከተማዋም ሁለተኛ ክፍል+ ዋይታ፣ከኮረብቶቹም ታላቅ ሁከት ይሰማል። 11  እናንተ የማክተሽ* ነዋሪዎች፣ ዋይ በሉ፤ነጋዴዎቹ ሁሉ እንዳልነበሩ ሆነዋልና፤*ብር የሚመዝኑትም ሁሉ ጠፍተዋል። 12  በዚያ ጊዜ ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ደግሞም ቸልተኛ የሆኑትንና*በልባቸው ‘ይሖዋ መልካምም ሆነ ክፉ ነገር አያደርግም’ የሚሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።+ 13  ሀብታቸው ይዘረፋል፤ ቤቶቻቸውም ይወድማሉ።+ ቤቶችን ይሠራሉ፤ ሆኖም አይኖሩባቸውም፤ወይንም ይተክላሉ፤ ሆኖም የወይን ጠጁን አይጠጡም።+ 14  ታላቁ የይሖዋ ቀን ቅርብ ነው!+ ቅርብ ነው፤ ደግሞም በፍጥነት እየቀረበ ነው!*+ የይሖዋ ቀን ድምፅ አስፈሪ* ነው።+ በዚያ ተዋጊው ይጮኻል።+ 15  ያ ቀን የታላቅ ቁጣ ቀን፣+የጭንቀትና የሥቃይ ቀን፣+የአውሎ ነፋስና የጥፋት ቀን፣የጨለማና የጭጋግ ቀን፣+የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ይሆናል፤+ 16  በተመሸጉ ከተሞችና በቅጥር ማዕዘኖች ላይ ባሉ ረጃጅም ማማዎች ላይ+የቀንደ መለከትና የጦርነት ሁካታ ድምፅ የሚሰማበት ቀን ይሆናል።+ 17  በሰዎች ላይ ጭንቀት አመጣለሁ፤እነሱም እንደ ዕውር ይሄዳሉ፤+ምክንያቱም በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርተዋል።+ ደማቸው እንደ አቧራ፣አንጀታቸውም እንደ ፋንድያ ይፈስሳል።+ 18  በይሖዋ ታላቅ ቁጣ ቀን ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤+መላዋ ምድር በቅንዓቱ እሳት ትበላለች፤+ምክንያቱም በምድር ላይ የሚኖሩትን ሁሉ በአሰቃቂ ሁኔታ ያጠፋቸዋል።”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

“ይሖዋ ሸሸገ (ተንከባከበ)” የሚል ትርጉም አለው።
ከጣዖት አምልኮ ጋር ንክኪ ያላቸውን ቁሳቁሶች ወይም ተግባሮች የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
ወይም “ርዝራዦች።”
ወይም “ደፉ።” የንጉሡን ዙፋን መድረክ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።
በዓሣ በር አቅራቢያ የሚገኝ ኢየሩሳሌም ውስጥ ያለ ቦታ ሳይሆን አይቀርም።
ቃል በቃል “ጸጥ ተደርገዋልና።”
ቃል በቃል “በአተላቸው ላይ የረጉትንና።” በወይን መጭመቂያ ውስጥ እንደሚሆነው ማለት ነው።
ወይም “እጅግ እየተቻኮለ ነው!”
ቃል በቃል “መራራ።”