ሚክያስ 7:1-20
7 ወዮልኝ! የበጋ ፍሬ* ከተሰበሰበናወይን የሚሰበሰብበት ጊዜ አብቅቶቃርሚያ ከተለቀመ በኋላየሚበላ የወይን ዘለላ እንደማያገኝ ሰው ሆኛለሁ፤በጣም የምመኘውን፣* በመጀመሪያው ወቅት የሚደርሰውን በለስም አላገኘሁም።
2 ታማኝ ሰው ከምድሪቱ ጠፍቷል፤*ከሰው ልጆችም መካከል ቅን የሆነ የለም።+
ሁሉም ደም ለማፍሰስ ያደባሉ።+
እያንዳንዱም የገዛ ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል።
3 እጆቻቸው መጥፎ ነገር በማድረግ የተካኑ ናቸው፤+ገዢው የሆነ ነገር እንዲደረግለት ይጠይቃል፤ፈራጁ ክፍያ ይጠይቃል፤+ታዋቂ የሆነው ሰው የራሱን ፍላጎት ይገልጻል፤*+እነሱም አንድ ላይ ሆነው ያሴራሉ።*
4 ከእነሱ መካከል የተሻለ የተባለው እንደ እሾህ ነው፤እጅግ ቅን የተባለው ደግሞ ከእሾህ ቁጥቋጦ የከፋ ነው።
ጠባቂዎችህ የተናገሩለት፣ አንተ የምትጎበኝበት ቀን ይመጣል።+
እነሱ አሁን ይሸበራሉ።+
5 ባልንጀራህን አትመን፤ወይም በቅርብ ወዳጅህ አትታመን።+
በእቅፍህ ለምትተኛው ስለምትናገረው ነገር ተጠንቀቅ።
6 ወንድ ልጅ አባቱን ይንቃልና፤ሴት ልጅ በእናቷ ላይ ትነሳለች፤+ምራት ደግሞ በአማቷ ላይ ትነሳለች፤+የሰው ጠላቶቹ ቤተሰቦቹ ናቸው።+
7 እኔ ግን ይሖዋን በጉጉት እጠባበቃለሁ።+
የሚያድነኝን አምላክ በትዕግሥት እጠብቃለሁ።*+
አምላኬ ይሰማኛል።+
8 ጠላቴ ሆይ፣ በእኔ ላይ በደረሰው ነገር ሐሴት አታድርጊ።
ብወድቅም እንኳ እነሳለሁ፤በጨለማ ውስጥ ብቀመጥም ይሖዋ ብርሃን ይሆንልኛል።
9 በእሱ ላይ ኃጢአት ስለሠራሁ+ለእኔ እስኪሟገትልኝና ፍትሕ እንዳገኝ እስከሚያደርግ ድረስየይሖዋን ቁጣ ችዬ እኖራለሁ።
እሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል፤እኔም የእሱን ጽድቅ አያለሁ።
10 “አምላክህ ይሖዋ የት አለ?”ስትለኝ የነበረችው ጠላቴም ታያለች፤
ኀፍረትም ትከናነባለች።+
ዓይኖቼም ያዩአታል።
በዚያን ጊዜ በጎዳና ላይ እንዳለ ጭቃ የምትረገጥ ቦታ ትሆናለች።
11 የድንጋይ ቅጥሮችሽ የሚገነቡበት ቀን ይሆናል፤በዚያ ቀን ድንበሩ ይሰፋል።*
12 በዚያ ቀን ከአሦርና ከግብፅ ከተሞች፣ከግብፅ አንስቶ እስከ ወንዙ* ድረስ፣ከባሕር እስከ ባሕር፣ ከተራራም እስከ ተራራ ድረስ ያሉ ሰዎችወደ አንቺ ይመጣሉ።+
13 ምድሪቱም ከነዋሪዎቿና ከሠሩት ነገር* የተነሳባድማ ትሆናለች።
14 ሕዝብህን ይኸውም በጫካ ውስጥ በፍራፍሬ እርሻ መካከል ብቻውን ያለውን፣የርስትህን መንጋ እንደ እረኛ በበትር ጠብቅ።+
እንደ ድሮው ዘመን በባሳንና በጊልያድ ይሰማሩ።+
15 “ከግብፅ ምድር በወጣችሁበት ዘመን እንደነበረውድንቅ ሥራዎችን አሳያችኋለሁ።+
16 ብሔራትም ያያሉ፤ ታላቅ ኃይል ቢኖራቸውም ያፍራሉ።+
እጃቸውን በአፋቸው ላይ ይጭናሉ፤ጆሯቸው ይደነቁራል።
17 እንደ እባብ አፈር ይልሳሉ፤+በምድር ላይ እንደሚሳቡ እንስሳት እየተንቀጠቀጡ ከምሽጎቻቸው ይወጣሉ።
በፍርሃት ተውጠው ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ ይመጣሉ፤አንተንም ይፈሩሃል።”+
18 የርስቱን ቀሪዎች+ ኃጢአት ይቅር የሚል፣ በደላቸውንም የሚያልፍእንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው?+
እሱ ለዘላለም አይቆጣም፤ታማኝ ፍቅር በማሳየት ደስ ይሰኛልና።+
19 ዳግመኛ ምሕረት ያሳየናል፤+ በደላችንን በቁጥጥሩ ሥር ያደርጋል።*
ኃጢአታቸውን ሁሉ ወደ ጥልቅ ባሕር ትጥላለህ።+
20 በጥንት ዘመን ለአባቶቻችን በማልክላቸው መሠረትለያዕቆብ ታማኝነትን፣ለአብርሃም ደግሞ ታማኝ ፍቅርን ታሳያለህ።+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ የበጋ ፍሬ በዋነኝነት የሚያመለክተው “በለስን” ሲሆን “ቴምርንም” ሊጨምር ይችላል።
^ ወይም “ነፍሴ በጣም የምትመኘውን።”
^ ወይም “ደብዛው ጠፍቷል።”
^ ወይም “የነፍሱን ምኞት ይገልጻል።”
^ ቃል በቃል “ይጎነጉናሉ።”
^ ወይም “በትዕግሥት የመጠበቅ ዝንባሌ አሳያለሁ።”
^ “ድንጋጌው ይርቃል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ኤፍራጥስን ያመለክታል።
^ ቃል በቃል “ከሥራቸው ፍሬ።”
^ ወይም “ይረግጣል፤ ያሸንፋል።”