ሚክያስ 5:1-15

  • በመላው ምድር ላይ ታላቅ የሚሆን ገዢ (1-6)

    • ከቤተልሔም የሚወጣ ገዢ (2)

  • የተረፉት እንደ ጠልና እንደ አንበሳ ይሆናሉ (7-9)

  • ምድሪቱ ትነጻለች (10-15)

5  “አንቺ ጥቃት የተሰነዘረብሽ ሴት ልጅ ሆይ፣አሁን ሰውነትሽን ትተለትያለሽ፤ዙሪያችንን ተከበናል።+ የእስራኤልን ፈራጅ ጉንጩን በዱላ ይመቱታል።+  2  ከይሁዳ አእላፋት* መካከል በጣም ትንሽ የሆንሽውቤተልሔም ኤፍራታ+ ሆይ፣ምንጩ ከጥንት፣ ከረጅም ዘመን በፊት የሆነ፣በእስራኤል ገዢ የሚሆን ከአንቺ ይወጣልኛል።+  3  ስለዚህ ልትወልድ የተቃረበችው ሴት እስክትወልድ ድረስአሳልፎ ይሰጣቸዋል። የቀሩት ወንድሞቹም ወደ እስራኤል ሕዝብ ይመለሳሉ።  4  እሱ በይሖዋ ብርታትና በአምላኩ በይሖዋ ስም ታላቅነት ይነሳል፤መንጋውንም እንደ እረኛ ይጠብቃል።+ እነሱም በዚያ ያለስጋት ይቀመጣሉ፤+በዚያን ጊዜ ታላቅነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርሳልና።+  5  እሱም ሰላም ያመጣል።+ አሦራዊው ምድራችንን ከወረረና የማይደፈሩ ማማዎቻችንን ከረገጠ+በእሱ ላይ ሰባት እረኞችን፣ አዎ ከሰው ልጆች መካከል ስምንት አለቆችን* እናስነሳበታለን።  6  እነሱ የአሦርን ምድር በሰይፍ ይቀጣሉ፤+የናምሩድንም+ ምድር መግቢያዎች ይቆጣጠራሉ። አሦራዊው ምድራችንን ሲወርና ክልላችንን ሲረግጥእሱ ይታደገናል።+  7  የተረፉት የያዕቆብ ወገኖች በብዙ ሕዝቦች መካከል፣ከይሖዋ ዘንድ እንደሚወርድናሰውን ተስፋ እንደማያደርግወይም የሰው ልጆችን እንደማይጠባበቅ ጠል፣በአትክልትም ላይ እንደሚወርድ ካፊያ ይሆናሉ።  8  በዱር እንስሳት መካከል እንዳለ አንበሳ፣በሚያልፍበት ጊዜ እየረጋገጠና እየሰባበረ እንደሚሄድ፣በበግ መንጎች መካከል እንዳለ ደቦል አንበሳ፣የተረፉት የያዕቆብ ወገኖችም በብሔራት፣በብዙ ሕዝቦችም መካከል እንዲሁ ይሆናሉ፤ሊያስጥል የሚችልም አይኖርም።  9  እጅህ ከባላጋራዎችህ በላይ ከፍ ከፍ ትላለች፤ጠላቶችህም ሁሉ ይወገዳሉ።” 10  “በዚያም ቀን” ይላል ይሖዋ፣“ፈረሶችህን ከመካከልህ አስወግዳለሁ፤ ሠረገሎችህንም አጠፋለሁ። 11  በምድርህ ላይ የሚገኙትን ከተሞች እደመስሳለሁ፤የተመሸጉ ስፍራዎችህንም ሁሉ አፈራርሳለሁ። 12  ጥንቆላህን አስወግዳለሁ፤*ከእንግዲህም አስማተኛ በመካከልህ አይኖርም።+ 13  የተቀረጹ ምስሎችህንና ዓምዶችህን ከመካከልህ አስወግዳለሁ፤ከእንግዲህም ወዲህ ለእጆችህ ሥራ አትሰግድም።+ 14  የማምለኪያ ግንዶችህንም* ከመካከልህ እነቅላለሁ፤+ከተሞችህንም እደመስሳለሁ። 15  ታዛዥ ያልሆኑትን ብሔራት፣በቁጣና በንዴት እበቀላለሁ።”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ጎሳዎች።”
ወይም “መሪዎችን።”
ቃል በቃል “ከእጅህ አስወግዳለሁ።”