ሚክያስ 1:1-16

  • በሰማርያና በይሁዳ ላይ የተላለፈ ፍርድ (1-16)

    • ኃጢአትና ዓመፅ ችግር አስከተለ (5)

1  በይሁዳ ነገሥታት+ በኢዮዓታም፣+ በአካዝና+ በሕዝቅያስ+ ዘመን ወደ ሞረሸታዊው ወደ ሚክያስ*+ የመጣው እንዲሁም ሚክያስ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም በራእይ ያየው የይሖዋ ቃል ይህ ነው።”+   “እናንተ ሕዝቦች ሁላችሁም ስሙ! ምድርና በውስጧ ያሉ ሁሉ፣ በትኩረት ያዳምጡ፤ይሖዋ ቅዱስ በሆነው ቤተ መቅደሱ ነው። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በእናንተ ላይ ይመሥክርባችሁ።+   እነሆ፣ ይሖዋ ከስፍራው ይወጣል፤ወደ ታች ወርዶ የምድርን ከፍ ያሉ ቦታዎች ይረግጣል።   በእሳት ፊት እንዳለ ሰምናበገደል ላይ እንደሚወርድ ውኃተራሮቹ ከሥሩ ይቀልጣሉ፤+ሸለቆዎቹም* ይሰነጠቃሉ።   ይህ ሁሉ የሆነው በያዕቆብ ዓመፅ፣በእስራኤልም ቤት ኃጢአት የተነሳ ነው።+ ለያዕቆብ ዓመፅ ተጠያቂው ማን ነው? ሰማርያ አይደለችም?+ በይሁዳ ለሚገኙት ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችስ ተጠያቂው ማን ነው?+ ኢየሩሳሌም አይደለችም?   ሰማርያን በሜዳ እንደሚገኝ የፍርስራሽ ክምር፣ወይን እንደሚተከልበትም ስፍራ አደርጋታለሁ፤ድንጋዮቿን ወደ ሸለቆ እወረውራለሁ፤*መሠረቶቿንም አራቁታለሁ።   የተቀረጹ ምስሎቿ በሙሉ ይደቅቃሉ፤+ለዝሙት አዳሪነቷ የተሰጧት ስጦታዎች ሁሉ በእሳት ይቃጠላሉ።*+ ጣዖቶቿን ሁሉ እደመስሳለሁ። እነዚህን ሁሉ ነገሮች የሰበሰበችው ለዝሙት አዳሪነቷ በተከፈላት ደሞዝ ነው፤አሁን ደግሞ እነዚህ ነገሮች በሌላ ቦታ ላሉ ዝሙት አዳሪዎች ክፍያ እንዲሆኑ ይወሰዳሉ።”   ከዚህ የተነሳ ዋይ ዋይ እላለሁ፤ ደግሞም አላዝናለሁ፤+ባዶ እግሬንና ራቁቴን እሄዳለሁ።+ እንደ ቀበሮዎች አላዝናለሁ፤እንደ ሰጎኖችም አለቅሳለሁ።   ቁስሏ ሊፈወስ አይችልም፤+እስከ ይሁዳ ድረስ ተሰራጭቷል።+ መቅሰፍቱ እስከ ሕዝቤ በር፣ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ተዛምቷል።+ 10  “በጌት አታውሩት፤ከቶም አታልቅሱ። በቤትአፍራ* በአፈር ላይ ተንከባለሉ። 11  የሻፊር ነዋሪዎች ሆይ፣ እርቃናችሁን ሆናችሁ በኀፍረት ተሻገሩ። የጻናን ነዋሪዎች አልወጡም። በቤትዔጼል ዋይታ ይኖራል፤ ለእናንተ ድጋፍ መስጠቱንም ያቆማል። 12  የማሮት ነዋሪዎች መልካም ነገርን ተጠባበቁ፤ይሁንና ከይሖዋ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም በር የወረደው ክፉ ነገር ነው። 13  የለኪሶ+ ነዋሪዎች ሆይ፣ ፈረሶቹን ከሠረገላው ጋር እሰሩ። ለጽዮን ሴት ልጅ የኃጢአት መጀመሪያ ነበራችሁ፤በእናንተ ውስጥ የእስራኤል ዓመፅ ተገኝቷልና።+ 14  ስለዚህ ለሞረሸትጋት የመሰነባበቻ ስጦታ ትሰጫለሽ። የአክዚብ ቤቶች ለእስራኤል ነገሥታት ማታለያ ነበሩ። 15  የማሬሻህ+ ነዋሪዎች ሆይ፣ ድል አድራጊውን* ገና አመጣባችኋለሁ።+ የእስራኤል ክብር እስከ አዱላም+ ድረስ ይመጣል። 16  ለምትወዷቸው ልጆቻችሁ ፀጉራችሁን ተቆረጡ፤ ራሳችሁንም ተላጩ። እንደ ንስር ተመለጡ፤ልጆቻችሁ በግዞት ተወስደውባችኋልና።”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ሚካኤል (“እንደ አምላክ ያለ ማን ነው?” የሚል ትርጉም አለው) ወይም ሚካያህ (“እንደ ይሖዋ ያለ ማን ነው?” የሚል ትርጉም አለው) የሚሉት ስሞች አጭር መጠሪያ።
ወይም “ረባዳማ ሜዳዎቹም።”
ቃል በቃል “ሸለቆ ውስጥ አፈሳለሁ።”
ወይም “የተከፈላት ደሞዝ ሁሉ በእሳት ይቃጠላል።”
ወይም “በአፍራ ቤት።”
ወይም “በዝባዡን።”