ሚልክያስ 4:1-6

  • ከይሖዋ ቀን በፊት ኤልያስ ይመጣል (1-6)

    • ‘የጽድቅ ፀሐይ ትወጣለች’ (2)

4  “እነሆ፣ ያ ቀን እንደ ምድጃ እየነደደ ይመጣል፤+ በዚያ ጊዜ እብሪተኞች ሁሉና ክፉ አድራጊዎች በሙሉ እንደ ገለባ ይሆናሉ። የሚመጣው ቀን በእርግጥ ይበላቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “ሥርም ሆነ ቅርንጫፍ አይተውላቸውም።  ስሜን ለምታከብሩት* ለእናንተ ግን የጽድቅ ፀሐይ በጨረሮቿ* ፈውስ ይዛ ትወጣለች፤ እናንተም እንደሰቡ ጥጆች ትቦርቃላችሁ።”  “እኔም እርምጃ በምወስድበት ቀን ክፉዎችን ትረግጣላችሁ፤ ከእግራችሁ ሥር እንዳለ አቧራ ይሆናሉና” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።  “የአገልጋዬን የሙሴን ሕግ ይኸውም መላው እስራኤል እንዲያከብረው በኮሬብ ያዘዝኩትን ሥርዓትና ድንጋጌ አስታውሱ።+  “እነሆ፣ ታላቁና የሚያስፈራው የይሖዋ ቀን ከመምጣቱ በፊት+ ነቢዩ ኤልያስን እልክላችኋለሁ።+  እሱም መጥቼ ምድርን እንዳልመታና ፈጽሜ እንዳላጠፋ የአባቶችን ልብ እንደ ልጆች ልብ፣+ የልጆችንም ልብ እንደ አባቶች ልብ ያደርጋል።”*

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “ለምትፈሩት።”
ቃል በቃል “በክንፎቿ።”
ወይም “የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፣ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።”