ሕዝቅኤል 15:1-8

  • ኢየሩሳሌም፣ የማትጠቅም የወይን ተክል (1-8)

15  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ የወይን ተክል እንጨት በጫካ ዛፎች መካከል ካለ ከየትኛውም ዛፍ ወይም ቅርንጫፍ ከተወሰደ እንጨት ጋር እንዴት ሊወዳደር ይችላል? 3  ከወይን ተክል የሚገኝ ግንድ ሥራ ላይ ሊውል ይችላል? ወይስ ሰዎች ግንዱን ተጠቅመው ዕቃ ለማንጠልጠል የሚያገለግል ኩላብ ይሠራሉ? 4  እነሆ፣ ማገዶ እንዲሆን እሳት ውስጥ ይጣላል፤ እሳቱ ጫፍና ጫፉን ይበላዋል፤ መሃሉንም ይለበልበዋል። ከዚህ በኋላ ሥራ ላይ ሊውል ይችላል? 5  ምንም ነገር ሳይነካውም እንኳ ለምንም ነገር ሊያገለግል አይችልም። እሳት ሲበላውና ሲለበልበውማ ጨርሶ ከጥቅም ውጭ ይሆናል!” 6  “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ማገዶ እንዲሆን ለእሳት አሳልፌ እንደሰጠሁት በጫካ ዛፎች መካከል እንዳለ የወይን ተክል እንጨት ሁሉ፣ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎችም ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ።+ 7  ፊቴን በእነሱ ላይ አድርጌአለሁ። ከእሳቱ ቢያመልጡም እሳት ይበላቸዋል። ፊቴንም በእነሱ ላይ በማደርግበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’”+ 8  “‘ታማኝ ሳይሆኑ በመቅረታቸውም+ ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”

የግርጌ ማስታወሻዎች