ሆሴዕ 8:1-14

  • ጣዖት አምልኮ የሚያስከትለው መዘዝ (1-14)

    • “ነፋስን ይዘራሉ፤ አውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ” (7)

    • “እስራኤል ፈጣሪውን ረስቷል” (14)

8  “ቀንደ መለከት ንፋ!+ ቃል ኪዳኔን ስላፈረሱና+ ሕጌን ስለጣሱ+በይሖዋ ቤት ላይ ጠላት እንደ ንስር ይመጣል።+   ‘አምላካችን ሆይ፣ እኛ የእስራኤል ሰዎች እናውቅሃለን!’ እያሉ ወደ እኔ ይጮኻሉ።+   እስራኤል መልካም የሆነውን ነገር ገሸሽ አድርጓል።+ ጠላት ያሳደው።   እኔ ሳልላቸው ነገሥታትን አነገሡ። መኳንንትን ሾሙ፤ እኔ ግን እውቅና አልሰጠኋቸውም። በገዛ ራሳቸው ላይ ጥፋት ለማምጣት+በብራቸውና በወርቃቸው ጣዖቶች ሠሩ።+   ሰማርያ ሆይ፣ የጥጃ ጣዖትሽ ተጥሏል።+ ቁጣዬ በእነሱ ላይ ይነዳል።+ ንጹሕ መሆን* የሚሳናቸው እስከ መቼ ነው?   ይህ ከእስራኤል ነውና። የእጅ ጥበብ ባለሙያ የሠራው ይህ ጥጃ አምላክ አይደለም፤የሰማርያ ጥጃ ተሰባብሮ እንዳልነበረ ይሆናል።   ነፋስን ይዘራሉ፤አውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ።+ አገዳው፣ የደረሰ ፍሬ* የለውም፤+እህሉ፣ ዱቄት አላስገኘም። ፍሬ ቢያፈራ እንኳ ባዕዳን* ይበሉታል።+   የእስራኤል ሰዎች ይዋጣሉ።+ በብሔራት መካከልማንም እንደማይፈልገው ዕቃ ይሆናሉ።+   ተገልሎ እንደሚኖር የዱር አህያ ወደ አሦር ሄደዋልና።+ ኤፍሬም በገንዘብ ፍቅረኞች አፍርቷል።+ 10  ፍቅረኞቻቸውን ያፈሩት ከብሔራት ቢሆንም፣እኔ አሁን እሰበስባቸዋለሁ፤ንጉሥና መኳንንት በጫኑባቸው ሸክም የተነሳ ሥቃይ ይደርስባቸዋል።+ 11  ኤፍሬም ኃጢአት ለመሥራት መሠዊያዎችን አብዝቷል።+ ኃጢአት የሚፈጽምባቸው መሠዊያዎች ሆነውለታል።+ 12  በሕጌ* ውስጥ ያለውን አብዛኛውን ነገር ጽፌለታለሁ፤እነሱ ግን እንግዳ ነገር አድርገው ቆጠሩት።+ 13  መሥዋዕቶችን ስጦታ አድርገው ለእኔ ያቀርባሉ፤ ሥጋውንም ይበላሉ፤ይሖዋ ግን በእነሱ አልተደሰተም።+ በደላቸውን ያስታውሳል፤ ለሠሯቸውም ኃጢአቶች ይቀጣቸዋል።+ እነሱ ወደ ግብፅ ተመልሰዋል።*+ 14  እስራኤል ፈጣሪውን ረስቷል፤+ ቤተ መቅደሶችንም ገንብቷል፤+ይሁዳም የተመሸጉ ከተሞችን አብዝቷል።+ እኔ ግን በከተሞቹ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤እሳቱም የእያንዳንዳቸውን ማማዎች ይበላል።”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ራሳቸውን ማንጻት።”
ወይም “ዛላ።”
ወይም “እንግዶች።”
ወይም “በመመሪያዬ፤ በትምህርቴ።”
“ይመለሳሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።