ሆሴዕ 4:1-19

  • ይሖዋ ከእስራኤል ጋር ይፋረዳል (1-8)

    • በምድሪቱ ላይ አምላክን ማወቅ የለም (1)

  • የእስራኤል የጣዖት አምልኮና ሴሰኝነት (9-19)

    • የአመንዝራነት መንፈስ እንዲባዝኑ ያደርጋል (12)

4  የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ይሖዋ ከምድሪቱ ነዋሪዎች ጋር ስለሚፋረድ የይሖዋን ቃል ስሙ፤+ምክንያቱም በምድሪቱ ላይ እውነት፣ ታማኝ ፍቅርና አምላክን ማወቅ የለም።+   የሐሰት መሐላ፣ ውሸት፣+ ነፍስ ግድያ፣+ስርቆትና ምንዝር+ ተስፋፍቷል፤ደም የማፍሰስ ወንጀልም በላይ በላዩ ይፈጸማል።+   ከዚህም የተነሳ ምድሪቱ ታዝናለች፤+በእሷም ላይ የሚኖሩ ሁሉ ይመነምናሉ፤የዱር እንስሳትና የሰማይ ወፎችየባሕር ዓሣዎችም እንኳ ሳይቀሩ ይጠፋሉ።   “ይሁን እንጂ ማንም ሰው አይሟገት ወይም ሌላውን አይውቀስ፤+ሕዝብህ ከካህን ጋር እንደሚሟገት ሰው ነውና።+   ስለዚህ እናንተ በጠራራ ፀሐይ ትሰናከላላችሁ፤የጨለመ ይመስል ነቢዩም ከእናንተ ጋር ይሰናከላል። እናታችሁንም ጸጥ አሰኛታለሁ።*   ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ይጠፋል። እናንተ እውቀትን ስለናቃችሁ+እኔም ካህናት ሆናችሁ እንዳታገለግሉኝ እንቃችኋለሁ፤የአምላካችሁን ሕግ* ስለረሳችሁ+እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።   እነሱ በበዙ ቁጥር በእኔ ላይ የሚሠሩት ኃጢአት በዝቷል።+ ክብራቸውን ወደ ውርደት እለውጣለሁ።*   የሕዝቤ ኃጢአት መብል ሆኖላቸዋል፤ደግሞም እነሱ በደል እንዲሠሩ ይቋምጣሉ።*   ሕዝቡንም ሆነ ካህኑንለተከተሉት መንገድ ተጠያቂ አደርጋቸዋለሁ፤አድራጎታቸው ያስከተለውንም መዘዝ በላያቸው አመጣለሁ።+ 10  ይበላሉ፤ ሆኖም አይጠግቡም።+ ሴሰኞች ይሆናሉ፤* ሆኖም ቁጥራቸው አይጨምርም፤+ምክንያቱም ይሖዋን ችላ ብለዋል። 11  ምንዝር፣* ያረጀ የወይን ጠጅና አዲስ የወይን ጠጅ፣ሰው ትክክል የሆነውን ነገር ለመፈጸም ያለውን ልባዊ ፍላጎት ያጠፋሉ።*+ 12  ሕዝቤ ከእንጨት የተሠሩ ጣዖቶቻቸውን ያማክራሉ፤በትራቸው* የሚላቸውን ነገር ያደርጋሉ፤ምክንያቱም የአመንዝራነት* መንፈስ እንዲባዝኑ ያደርጋቸዋል፤በአመንዝራነታቸው* የተነሳም ለአምላካቸው ለመገዛት አሻፈረን ይላሉ። 13  በተራሮች አናት ላይ ይሠዋሉ፤+ደግሞም በኮረብቶች ላይእንዲሁም በባሉጥ ዛፎች፣ በሊብነህ ዛፎችና* በትልቅ ዛፍ ሁሉ ሥር የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርባሉ፤+ምክንያቱም የዛፎቹ ጥላ መልካም ነው። ከዚህም የተነሳ ሴቶች ልጆቻችሁ ዝሙት አዳሪዎች* ይሆናሉ፤ምራቶቻችሁም ያመነዝራሉ። 14  ሴቶች ልጆቻችሁ ዝሙት አዳሪዎች* በመሆናቸው፣ምራቶቻችሁም በማመንዘራቸው አልቀጣቸውም። ወንዶቹ ከጋለሞታዎች ጋር ተያይዘው ይሄዳሉና፤ከቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪዎችም ጋር መሥዋዕት ያቀርባሉ፤እንዲህ ያለ ማስተዋል የሌለው ሕዝብ+ ይጠፋል። 15  እስራኤል ሆይ፣ አንቺ ብታመነዝሪም*+ይሁዳ ግን ተመሳሳይ በደል አትፈጽም።+ ወደ ጊልጋል+ ወይም ወደ ቤትአዌን+ አትሂዱ፤‘ሕያው ይሖዋን!’ ብላችሁም አትማሉ።+ 16  እስራኤል እንደ እልኸኛ በሬ እልኸኛ ሆናለችና።+ ታዲያ ይሖዋ እንደ በግ ጠቦት በተንጣለለ የግጦሽ መስክ* ያሰማራቸዋል? 17  ኤፍሬም ከጣዖቶች ጋር ተቆራኝቷል።+ በቃ ተዉት! 18  መጠጣቸው* ሲያልቅሴሰኞች ይሆናሉ።* ገዢዎቿም* ነውርን አጥብቀው ይወዳሉ።+ 19  ነፋስ በክንፎቹ ይጠቀልላታል፤*እነሱም ባቀረቧቸው መሥዋዕቶች ያፍራሉ።”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “እናታችሁንም አጠፋታለሁ።”
ወይም “መመሪያ፤ ትምህርት።”
“ክብሬን በውርደት ለውጠዋል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ነፍሳቸው ትመኛለች።” የቃላት መፍቻው ላይ “ነፍስ” የሚለውን ተመልከት።
ወይም “እጅግ ነውረኛ ይሆናሉ፤ ያመነዝራሉ።”
ወይም “ነውረኝነት፤ ሴሰኝነት።”
ቃል በቃል “ልብ ያጠፋሉ።”
ወይም “የሟርተኛ ዘንጋቸው።”
ወይም “የነውረኝነት፤ የሴሰኝነት።”
ወይም “በነውረኝነታቸው፤ በሴሰኝነታቸው።”
ጥሩ መዓዛ ያላቸው ነጫጭ አበቦች የሚያወጣ ዛፍ።
ወይም “ነውረኞች፤ ሴሰኞች።”
ወይም “ነውረኞች፤ ሴሰኞች።”
ወይም “ነውር ብትፈጽሚም፤ ብትሴስኚም።”
ቃል በቃል “ሰፊ በሆነ ስፍራ።”
ወይም “ከስንዴ የሚዘጋጅ መጠጣቸው።”
ወይም “እጅግ ነውረኛ ይሆናሉ፤ ያመነዝራሉ።”
ቃል በቃል “ጋሻዎቿም።”
ወይም “ጠራርጎ ይወስዳታል።”