ሆሴዕ 3:1-5

  • ሆሴዕ አመንዝራ የሆነችውን ሚስቱን መልሶ ወሰዳት (1-3)

  • እስራኤላውያን ተመልሰው ወደ ይሖዋ ይመጣሉ (4, 5)

3  ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሌሎች አማልክትን የሚከተሉና+ የዘቢብ ቂጣ* የሚወዱ ሆነው ሳለ ይሖዋ እንደወደዳቸው ሁሉ፣+ አንተም ሄደህ በሌላ ሰው የተወደደችውንና ምንዝር የምትፈጽመውን ሴት ዳግመኛ ውደዳት።”+  በመሆኑም በ15 የብር ሰቅልና በአንድ ተኩል የሆሜር* መስፈሪያ ገብስ ለራሴ ገዛኋት።  ከዚያም እንዲህ አልኳት፦ “ለብዙ ቀናት የእኔ ሆነሽ ትቀመጫለሽ። አታመንዝሪ፤* ከሌላ ሰውም ጋር ግንኙነት አታድርጊ፤ እኔም ከአንቺ ጋር ግንኙነት አልፈጽምም።”  ምክንያቱም የእስራኤል ሕዝብ ለረጅም ጊዜ ያለንጉሥ፣+ ያለገዢ፣ ያለመሥዋዕት፣ ያለዓምድ፣ ያለኤፉድና+ ያለተራፊም ምስል*+ ይኖራሉ።  ከዚያም በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ተመልሰው አምላካቸውን ይሖዋንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤+ በዘመኑም መጨረሻ ወደ ይሖዋና ወደ ጥሩነቱ እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ለሐሰት አምልኮ የሚጠቀሙበትን ቂጣ ያመለክታል።
አንድ ሆሜር 220 ሊትር ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ነውር አትፈጽሚ (አትሴስኚ)።”
ወይም “የቤት ውስጥ አማልክት፤ ጣዖታት።”