ሆሴዕ 11:1-12

  • “እስራኤል ገና ልጅ ሳለ ወደድኩት” (1-12)

    • ‘ልጄን ከግብፅ ጠራሁት’ (1)

11  “እስራኤል ገና ልጅ ሳለ ወደድኩት፤+ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት።+   እነሱ* ደጋግመው በጠሯቸው መጠንበዚያው ልክ ከእነሱ ራቁ።+ ለባአል ምስሎች መሠዋታቸውን፣+ለተቀረጹት ምስሎችም መሥዋዕት ማቅረባቸውን ቀጠሉ።+   እኔ ግን ኤፍሬምን መራመድ አስተማርኩት፤+ በክንዶቼም ተሸከምኳቸው፤+የፈወስኳቸውም እኔ እንደሆንኩ አምነው አልተቀበሉም።   በሰዎች ገመድ፣* በፍቅርም ማሰሪያ ሳብኳቸው፤+ደግሞም ከጫንቃቸው ላይ* ቀንበር እንደሚያነሳ ሰው ሆንኩላቸው፤ለእያንዳንዳቸውም በደግነት ምግብ አቀረብኩላቸው።   እነሱ ወደ ግብፅ ምድር አይመለሱም፤ ሆኖም አሦር ንጉሣቸው ይሆናል፤+ምክንያቱም ወደ እኔ ለመመለስ አሻፈረን ብለዋል።+   በጠነሰሱት ሴራ የተነሳ በከተሞቹ ላይ ሰይፍ ያንዣብባል፤+መቀርቀሪያዎቹንም ይሰባብራል፤ ይበላቸዋልም።+   ሕዝቤ በእኔ ላይ ክህደት ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም።+ ወደ ላይ* ቢጠሯቸውም ማንም አይነሳም።   ኤፍሬም ሆይ፣ እንዴት ልተውህ እችላለሁ?+ እስራኤል ሆይ፣ እንዴት አሳልፌ ልሰጥህ እችላለሁ? እንዴትስ እንደ አድማህ አደርግሃለሁ? ደግሞስ እንዴት እንደ ጸቦይም ላደርግህ እችላለሁ?+ ስለ አንተ ያለኝ አመለካከት ተለወጠ፤የርኅራኄ ስሜቴም ተቀሰቀሰ።*+   የሚነድ ቁጣዬን አልገልጽም። ኤፍሬምን ዳግመኛ አላጠፋም፤+እኔ አምላክ እንጂ ሰው አይደለሁምና፤በመካከልህ ያለሁ ቅዱስ አምላክ ነኝ፤በአንተም ላይ በቁጣ አልመጣም። 10  እነሱ ይሖዋን ተከትለው ይሄዳሉ፤ እሱም እንደ አንበሳ ያገሳል፤+እሱ ሲያገሳ ልጆቹ ከምዕራብ እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ።+ 11  ከግብፅ ሲወጡ እንደ ወፍ፣ከአሦርም ምድር ሲወጡ እንደ ርግብ ይርገፈገፋሉ፤+እኔም በየቤታቸው እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ” ይላል ይሖዋ።+ 12  “ኤፍሬም በውሸት፣የእስራኤልም ቤት በማታለል ከበበኝ።+ ይሁዳ ግን አሁንም ከአምላክ ጋር ይሄዳል፤*እጅግ ቅዱስ ለሆነውም አምላክ ታማኝ ነው።”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

እስራኤልን ለማስተማር የተላኩትን ነቢያትና ሌሎች ሰዎች ያመለክታል።
ወይም “በደግነት ገመድ።” አንድ ወላጅ የሚጠቀምበትን ገመድ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “ከመንጋጋቸው።”
ላቅ ያለ አምልኮን ያመለክታል።
ቃል በቃል “ግሏል።”
ወይም “ከአምላክ ጋር ይዞራል።”