በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መግቢያ

መግቢያ

ከትዳርና ከቤተሰብ ሕይወት ጋር በተያያዘ ብዙ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ባሉበት በዚህ አስጨናቂ ዘመን የቤተሰብን ሕይወት አስደሳች ማድረግ ይቻላል? ይህን ማድረግ ቀላል አይደለም። ሆኖም በዚህ ረገድ እገዛ ማግኘት ይቻላል። ይህ ብሮሹር ትዳርን አስደሳች ለማድረግ የሚረዳ የተሟላ መመሪያ ባይዝም አስተማማኝ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችንና ጠቃሚ የሆኑ ሐሳቦች ያጎላል። የቀረቡትን ሐሳቦች ተግባራዊ ማድረጋችሁ አስደሳች የቤተሰብ ሕይወት እንዲኖራችሁ አስተዋጽኦ ያደርጋል።