ጥሩ ውጤት ማምጣት የምችለው እንዴት ነው?
ምዕራፍ 13
ጥሩ ውጤት ማምጣት የምችለው እንዴት ነው?
መውጫ በሌለው ጥቅጥቅ ያለ ደን ውስጥ እንዳለህ አድርገህ አስብ። ዛፎቹ ችምችም ያሉ በመሆናቸው የፀሐይ ብርሃን እንኳ ማግኘት አስቸጋሪ ሆኖብሃል። ዙሪያህ በዕፅዋት የተሸፈነ በመሆኑ እንደ ልብህ መንቀሳቀስ አልቻልክም። ከዚህ ቦታ ለመውጣት የሚያስችል መንገድ ለማግኘት ከፊትህ ያሉትን ዕፅዋት በቆንጨራ መመንጠር ይኖርብሃል።
አንዳንዶች የትምህርት ቤት ሕይወታቸው ከላይ ከተጠቀሰው ሁኔታ ጋር እንደሚመሳሰል ይሰማቸዋል። እነዚህ ልጆች መውጫ የሌለው ጫካ ውስጥ የገቡ ያህል ቀኑን ሙሉ በትምህርት ቤት ታስረው ይውላሉ፤ ማታ ደግሞ ለረጅም ሰዓታት የቤት ሥራቸው ላይ ተተክለው ስለሚያመሹ መፈናፈኛ የላቸውም። አንተስ እንደዚህ ይሰማሃል? በጣም የሚከብድህን የትምህርት ዓይነት ከታች ባለው ክፍት ቦታ ላይ ጻፍ።
․․․․․
ምናልባትም ወላጆችህና አስተማሪዎችህ ይህን የትምህርት ዓይነት በርትተህ እንድታጠና ደጋግመው ይመክሩህ ይሆናል። ይህን የሚያደርጉት ግን ሊያስጨንቁህ ፈልገው አይደለም! ከዚህ ይልቅ ችሎታህን ሙሉ በሙሉ እንድትጠቀምበት አስበው ነው። ይሁንና ግፊቱ ከመብዛቱ የተነሳ የምታደርገውን ጥረት እርግፍ አድርገህ ለመተው አስበህ ይሆን? ከሆነ ምን ማድረግ ትችላለህ? ትክክለኛው መሣሪያ ካለህ፣ ጥቅጥቅ ካለ ደን ጋር ከሚመሳሰለው ከዚህ ሁኔታ ለመውጣት መንገድ ማግኘት ትችላለህ። በዚህ ረገድ የሚረዱህ መሣሪያዎች ምንድን ናቸው?
● መሣሪያ 1፦ ለትምህርት አዎንታዊ አመለካከት ይኑርህ። ለትምህርት ተገቢ አመለካከት ከሌለህ በትምህርት ቤት ጥሩ ውጤት ለማምጣት አትነሳሳም። ስለዚህ ጉዳዩን ሰፋ አድርግህ ለመመልከት ሞክር። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “አራሹ ድርሻ እንደሚኖረው ተስፋ በማድረግ እንዲያርስ፣ የሚያበራየውም ድርሻ እንደሚኖረው ተስፋ በማድረግ እንዲያበራይ ነው።”—1 ቆሮንቶስ 9:10
አንድ አራሽ ጠንክሮ እንዲሠራ የሚያነሳሳው ጥሩ ውጤት እንደሚያገኝ ያለው ተስፋ ነው። አንተ ግን አንዳንድ የትምህርት ዓይነቶችን በደንብ ለማወቅ ቁፈራ ማድረግህ የሚያስገኘው ጥቅም በቀላሉ አይታይህ 1 ቆሮንቶስ 9:22) ሌላው ቢቀር የማመዛዘን ችሎታህን ያሻሽልልሃል፤ ይህ ደግሞ ለወደፊት ሕይወትህ እንደሚጠቅምህ ምንም ጥርጥር የለውም።
ይሆናል። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? በሥርዓተ ትምህርቱ ውስጥ ከተካተቱት የትምህርት ዓይነቶች አንዳንዶቹ ቢያንስ ለአሁኑ ሕይወትህ እንደማይጠቅሙህ ይሰማህ ይሆናል። ያም ቢሆን ስለተለያዩ የትምህርት ዓይነቶች እውቀት መቅሰምህ በዙሪያህ ስላለው ዓለም ግንዛቤህን ያሰፋልሃል። ይህም “ለሁሉም ዓይነት ሰዎች ሁሉንም ነገር [መሆን]” እንድትችል ስለሚረዳህ የተለያየ ባሕልና አስተዳደግ ካላቸው ሰዎች ጋር ለመግባባት ያስችልሃል። (● መሣሪያ 2፦ ላሉህ ችሎታዎች ተገቢ አመለካከት ይኑርህ። በትምህርት ቤት የምትቀስመው ትምህርት የተደበቁ ተሰጥኦዎችህን ለማወቅ ሊረዳህ ይችላል። ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ “የተቀበልከውን የአምላክ ስጦታ እንደ እሳት እንድታቀጣጥል አሳስብሃለሁ” በማለት ጽፎለታል። (2 ጢሞቴዎስ 1:6) ጢሞቴዎስ በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ልዩ የአገልግሎት መብት እንደነበረው ግልጽ ነው። ሆኖም ከአምላክ ያገኘው ችሎታ ወይም “ስጦታ” በውስጡ ታፍኖ እንዳይቀር ወይም እንዳይባክን ሊያዳብረው ይገባ ነበር። እርግጥ ነው፣ በትምህርት ቤት የሚኖርህ ችሎታ በቀጥታ ከአምላክ ያገኘኸው ስጦታ አይደለም። ያም ቢሆን ከሌሎች የተለየ የራስህ የሆነ ተሰጥኦ አለህ። ትምህርት ቤት መግባትህ ከዚህ በፊት ያላስተዋልካቸው በውስጥህ የተቀበሩ አንዳንድ ችሎታዎች እንዳሉህ እንድታውቅና እነዚህን ችሎታዎች እንድታዳብራቸው ሊረዳህ ይችላል።
2 ቆሮንቶስ 10:10፤ 11:6) ጳውሎስ ያሉበትን ድክመቶች ተገንዝቦ ነበር። ይሁንና ጠንካራ ጎኖችም እንዳሉት ያውቅ ነበር።
ችሎታህን ልታሻሽለው እንደማትችል ማሰብህ በትምህርትህ ጥሩ ውጤት እንዳታመጣ እንቅፋት ስለሚሆንብህ እንዲህ ያለውን አመለካከት አስወግድ። ‘ችሎታ የለኝም’ የሚል አፍራሽ አመለካከት የሚያስቸግርህ ከሆነ ይህን ስሜትህን በአዎንታዊ አስተሳሰብ ለመተካት ጥረት አድርግ። ለምሳሌ ያህል፣ አንዳንድ ሰዎች በጳውሎስ የመናገር ችሎታ ላይ ትችት (መሠረት የሌለው ሊሆን ይችላል) በሰነዘሩበት ወቅት ሐዋርያው እንዲህ የሚል ምላሽ ሰጥቷል፦ “የተዋጣልኝ ተናጋሪ ባልሆን እንኳ እውቀት የሚጎድለኝ ግን አይደለሁም።” (አንተስ? ምን ጠንካራ ጎኖች አሉህ? ጠንካራ ጎኖች እንደሌሉህ ከተሰማህ ስለ አንተ ለሚያስብ አንድ ትልቅ ሰው ስለዚህ ጉዳይ ለምን ጥያቄ አታቀርብለትም? እንዲህ ያለው ወዳጅ ጠንካራ ጎኖችህን ለይተህ እንድታውቅና በደንብ እንድትጠቀምባቸው ሊረዳህ ይችላል።
● መሣሪያ 3፦ ጥሩ የጥናት ልማድ አዳብር። በትምህርት ቤት ውጤታማ ለመሆን አቋራጭ መንገድ የለውም። በዚያም ሆነ በዚህ ማጥናት ይኖርብሃል። እርግጥ ነው፣ ማጥናት የሚለው ሐሳብ ገና ሲነሳ ጭንቅ ይልህ ይሆናል። ይሁን እንጂ ጥናት ጠቃሚ ነገር ነው። እንዲያውም የተወሰነ ጥረት ካደረግህ ጥናት አስደሳች ሊሆንልህ ይችላል።
እርግጥ ነው፣ ጥሩ የጥናት ልማድ መክብብ 3:1, 4፤ 11:9) ብዙ ወጣቶች እንደሚያደርጉት አንተም ለመዝናኛ ጊዜ መመደብ ትፈልግ ይሆናል። * ይሁንና “ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፤ ደመናትንም የሚያይ አያጭድም” የሚለውን በመክብብ 11:4 ላይ የሚገኘውን ማሳሰቢያ ልብ ማለት ይገባሃል። ከዚህ የምታገኘው ትምህርት ምንድን ነው? ጥናት ከጨዋታ ሊቀድም ይገባል። በዚህ ረገድ ሐሳብ አይግባህ፣ ለሁለቱም ጊዜ ማግኘት ትችላለህ!
ለማዳበር ጊዜህን በፕሮግራም መጠቀም ያስፈልግሃል። ተማሪ እስከሆንክ ድረስ ቅድሚያ ልትሰጠው የሚገባው ነገር ጥናት እንደሆነ አስታውስ። እውነት ነው፣ መጽሐፍ ቅዱስ “ለመሣቅም ጊዜ አለው . . . ለጭፈራም ጊዜ አለው” ይላል። (የቤት ሥራህ
የቤት ሥራ እየተቆለለብህ ትቸገራለህ? ምናልባት አንተም ሳንድሪን እንደተባለችው የ17 ዓመት ወጣት ይሰማህ ይሆናል፤ ሳንድሪን “ቅዳሜና እሁድን
ሳይጨምር በየምሽቱ ብቻ የቤት ሥራዬን በመሥራት ከሁለት እስከ ሦስት ሰዓት አጠፋለሁ” ብላለች። ታዲያ ይህን ሁኔታ ለመቋቋም ምን ማድረግ ትችላለህ? በገጽ 119 ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች ተግባራዊ ለማድረግ ሞክር።መሰናክሎቹን ማስወገድ
ጳውሎስ መንፈሳዊ እድገት ስለማድረግ ለጢሞቴዎስ ምክር ሲሰጠው እንዲህ በማለት ጽፏል፦ “እድገትህ በሁሉም ሰዎች ዘንድ በግልጽ እንዲታይ በእነዚህ ነገሮች ላይ አሰላስል፤ እንዲሁም ትኩረትህ ሙሉ በሙሉ በእነዚህ ነገሮች ላይ ያረፈ ይሁን።” (1 ጢሞቴዎስ 4:15) አንተም በተመሳሳይ ትጋት የተሞላበት ጥረት ካደረግህ በትምህርትህ የምታደርገው እድገት በግልጽ ይታያል።
በዚህ ምዕራፍ መግቢያ ላይ የቀረበውን ምሳሌ አስብ። ጥቅጥቅ ካለው ደን ውስጥ ለመውጣት እንድትችል ከፊትህ ያለውን መሰናክል ለማስወገድ የሚረዳህ ተስማሚ መሣሪያ ይኸውም ቆንጨራ ያስፈልግሃል። ከትምህርት ቤት ጋር በተያያዘም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው። ወላጆችህና አስተማሪዎችህ ስለሚጠብቁብህ ነገር እያሰብክ በጭንቀት ከመዋጥ ይልቅ በትምህርት ቤት ውጤታማ እንድትሆን የሚረዱህን በዚህ ምዕራፍ ላይ የቀረቡትን ሦስት መሣሪያዎች ተጠቀምባቸው። ውጤትህ እየተሻሻለ ሲመጣ በእነዚህ መሣሪያዎች በመጠቀምህ ትደሰታለህ!
ተጨማሪ ሐሳብ ለማግኘት የዚህን መጽሐፍ ጥራዝ 1 ምዕራፍ 18 ተመልከት
በትምህርት ቤት የሚያጋጥሙህ በርካታ ችግሮች እንዳይበቁህ ልጆቹ ደግሞ ያስቸግሩሃል። ይህን ሁኔታ ለመቋቋም ምን ማድረግ ትችላለህ?
[የግርጌ ማስታወሻ]
ቁልፍ ጥቅስ
“ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፤ ደመናትንም የሚያይ አያጭድም።”—መክብብ 11:4
ጠቃሚ ምክር
ለጥናት በምትዘጋጅበት ጊዜ መጀመሪያ የምታጠናውን ነገር አጠቃላይ ይዘት ለማወቅ ገረፍ ገረፍ አድርገህ እየው። ከዚያም በእያንዳንዱ ዋና ርዕስ ላይ ተመሥርተህ ጥያቄዎች አውጣ። ቀጥለህ ደግሞ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት የምታጠናውን ትምህርት አንብበው። በመጨረሻም ያነበብከውን ነገር ለማስታወስ ሞክር።
ይህን ታውቅ ነበር?
መኮረጅ በሌሎች ዘንድ ተአማኒነት እንድታጣና በትምህርትህ ደካማ እንድትሆን ያደርግሃል። ከምንም በላይ ደግሞ ከአምላክ ጋር ያለህ ዝምድና እንዲበላሽ ያደርጋል።—ምሳሌ 11:1
ላደርጋቸው ያሰብኳቸው ነገሮች
በሚቀጥለው ሴሚስተር ________ በማምጣት ላሻሽለው የምፈልገው የትምህርት ዓይነት ․․․․․
በዚህ የትምህርት ዓይነት ውጤቴን ለማሻሻል እንዲህ አደርጋለሁ፦ ․․․․․
ከዚህ ርዕሰ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ወላጆቼን ልጠይቃቸው የምፈልገው ነገር ․․․․․
ምን ይመስልሃል?
● ትምህርትህን በትጋት ማጥናት ያለብህ ለምንድን ነው?
● ትምህርትህን ለማጥናት/የቤት ሥራህን ለመሥራት የምትመርጠው ጊዜ የትኛው ነው?
● ቤት ስትሆን የቤት ሥራህን ለመሥራትና ለማጥናት አመቺ የሆነው ስፍራ የትኛው ነው?
● የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎችና መዝናኛዎች በትምህርት ውጤትህ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳያሳድሩ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
[በገጽ 117 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]
እኩዮቼ በሆኑ ወጣቶች ላይ እንዲህ ዓይነት አዝማሚያ እመለከታለሁ። በትምህርት ቤት ሕይወታቸው የሚከተሉት የጥናት ልማድ ከመንፈሳዊ ሕይወታቸው ጋር በተያያዘ በሚያከናውኑት የግል ጥናት ላይም ይንጸባረቃል። በትምህርት ቤት ማጥናት የማይወዱ ልጆች መጽሐፍ ቅዱስን በግላቸው ማጥናትም ያን ያህል አያስደስታቸውም።”—ሲልቪ
[በገጽ 119 ላይ የሚገኝ ሣጥን/ሥዕል]
የምታጠናበት ቦታ ምረጥ። ጸጥ ያለ ቦታ ሊሆን ይገባል። ከተቻለ ማጥኛ ጠረጴዛ ይኑርህ። እያጠናህ ቴሌቪዥን አትክፈት።
ቅድሚያ ለሚገባው ቅድሚያ ስጥ። ትምህርትህ በጣም አስፈላጊ ነገር ስለሆነ የቤት ሥራህን እስክትጨርስ ድረስ ቴሌቪዥን ላለመክፈት ቁርጥ ውሳኔ አድርግ።
ዛሬ ነገ አትበል። የቤት ሥራህን የምትሠራበት ቋሚ ፕሮግራም ይኑርህ፤ እንዲሁም ፕሮግራምህን በጥብቅ ተከተል።
እቅድ አውጣ። የትኛውን የቤት ሥራ መጀመሪያ መሥራት እንዳለብህ የትኛውን ደግሞ ቀጥለህ እንደምትሠራ ወስን። የቤት ሥራዎችህን የምትሠራበትን ቅደም ተከተል ወረቀት ላይ ካሰፈርክ በኋላ ለእያንዳንዱ የተወሰነ ጊዜ መድብ። እያንዳንዱን የቤት ሥራ ስታጠናቅቅ ወረቀቱ ላይ ምልክት አድርግ።
በየመሃሉ እረፍት አድርግ። ትኩረትህን መሰብሰብ ካቃተህ የምትሠራውን አቁመህ ለጥቂት ጊዜ እረፍት አድርግ። ሆኖም በተቻለ መጠን ቶሎ ወደ ቤት ሥራህ መመለስ ይኖርብሃል።
በራስህ ተማመን። አብዛኛውን ጊዜ ጎበዝ ወይም ሰነፍ ተማሪ መሆን የጭንቅላት ጉዳይ ሳይሆን ተግቶ የማጥናት ወይም ያለማጥናት ጉዳይ መሆኑን አስታውስ። አንተም በትምህርት ቤት ጥሩ ውጤት ማምጣት ትችላለህ። ትጋት የተሞላበት ጥረት ካደረግህ የድካምህን ፍሬ ታገኛለህ።
[በገጽ 116 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
የትምህርት ቤት ሕይወትን ማለፍ ጥቅጥቅ ካለ ደን ለመውጣት የሚያስችል መንገድ ከመክፈት ጋር ሊመሳሰል ይችላል፤ ትክክለኛውን መሣሪያ ከተጠቀምክ ግን ሁለቱንም በተሳካ ሁኔታ መወጣት ትችላለህ