ከግብረ ሰዶም መራቅ የምችለው እንዴት ነው?
ምዕራፍ 28
ከግብረ ሰዶም መራቅ የምችለው እንዴት ነው?
“በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ እያለሁ ለሌሎች ወንዶች የሚሰማኝን የፍቅር ስሜት ለማሸነፍ እታገል ነበር። እንዲህ ያለው ስሜት ትክክል እንዳልሆነ ልቤ ያውቀው ነበር።”—ጆን
“ከአንዲት ጓደኛዬ ጋር አንድ ሁለት ጊዜ ተሳስመን እናውቃለን። ለወንዶችም የፍቅር ስሜት ስለነበረኝ ‘ለሴቶችም ለወንዶችም የፆታ ፍላጎት አለኝ ማለት ነው?’ ብዬ አስብ ነበር።”—ሣራ
ከጥቂት አሥርተ ዓመታት በፊት ከነበረው ይልቅ ዛሬ ግብረ ሰዶም ይበልጥ ተቀባይነት እንዳገኘ ማንም አይክድም። ግብረ ሰዶምን እንደሚቃወም በገሃድ ለመናገርም ቢሆን የሚደፍር የለም ማለት ይቻላል! እንዲህ ብታደርግ ከየአቅጣጫው ትችት ሊሰነዘርብህ ይችላል። የ16 ዓመቷ ኤሚ እንዲህ ብላለች፦ “አንዲት ልጅ ዘረኛ እንደሆንኩ እንደሚሰማት ነገረችኝ፤ ይህን ያለችው ስለ ግብረ ሰዶም ያለኝ አመለካከት ሌላ ዘር ላላቸው ሰዎች ጭፍን ጥላቻ ከማሳየት ተለይቶ እንደማይታይ ስለተሰማት ነበር!”
በሥነ ምግባር ረገድ ልቅ የሆነው ይህ ዓለም የሚያሳድረው ተጽዕኖ በርካታ ወጣቶች ግብረ ሰዶም ለመፈጸም እንዲነሳሱ አድርጓቸዋል። የ15 ዓመት ወጣት የሆነችው ቤኪ እንዲህ ትላለች፦ “በምማርበት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኙ በርካታ ሴቶች ልጆች ሌዝቢያን እንደሆኑ [ከሴቶች ጋር የፆታ ግንኙነት እንደሚፈጽሙ] ወይም ከሁለቱም ፆታዎች ጋር የፆታ ግንኙነት እንደሚፈጽሙ አሊያም እንዲህ ማድረግ የሚፈጥረውን ስሜት የማወቅ ጉጉት እንዳላቸው ይናገራሉ።” የ18 ዓመት ወጣት የሆነችው ክሪስታም በትምህርት ቤቷ ውስጥ ተመሳሳይ ሁኔታ እንዳለ ትናገራለች። “አብረውኝ የሚማሩ ሁለት ሴት ልጆች ከእነሱ ጋር የፆታ ግንኙነት እንድፈጽም ጠይቀውኝ ነበር” ብላለች። “እንዲያውም አንዷ ከሴት ጋር የፆታ ግንኙነት መፈጸም ምን እንደሚመስል ማየት እፈልግ እንደሆነ ወረቀት ጽፋ ጠይቃኛለች።”
ተመሳሳይ ፆታ ባላቸው ሰዎች መካከል የሚፈጸም የፆታ ግንኙነት በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ያለው በመሆኑ የሚከተሉት ጥያቄዎች ወደ አእምሮህ ይመጡ ይሆናል፦ ‘ግብረ ሰዶም መፈጸም ያን ያህል ከባድ ነገር ነው? እንደ እኔ ዓይነት ፆታ ላለው ሰው የፍቅር ስሜት ቢያድርብኝስ? ግብረ ሰዶማዊ ነኝ ማለት ነው?’
አምላክ ግብረ ሰዶምን እንዴት ይመለከተዋል?
በዛሬው ጊዜ፣ አንዳንድ ሃይማኖታዊ መሪዎችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ግብረ ሰዶምን አቅልለው ይመለከቱታል። ሆኖም የአምላክ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ረገድ የሚሰጠው ሐሳብ ምንም የሚያሻማ አይደለም። ይሖዋ አምላክ ሰዎችን ወንድና ሴት አድርጎ እንደፈጠራቸው እንዲሁም የፆታ ግንኙነት በባልና ሚስት መካከል ብቻ እንዲፈጸም ዓላማው እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (ዘፍጥረት 1:27, 28፤ 2:24) በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ ግብረ ሰዶምን ማውገዙ ምንም አያስደንቅም።—ሮም 1:26, 27
እርግጥ ነው፣ አንዳንዶች የአምላክ ቃል ጊዜ ያለፈበት እንደሆነ ይናገራሉ። ሆኖም እንዲህ ያለ መደምደሚያ ላይ ለመድረስ የሚጣደፉት ለምን ይመስልሃል? መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ሐሳብ ከእነሱ አስተሳሰብ ጋር ስለሚጋጭ አይመስልህም? ብዙዎች የአምላክን ቃል የማይቀበሉት እነሱ ለማመን ከሚፈልጉት የተለየ ነገር ስለሚያስተምር ነው። ይሁንና የአምላክ ቃል ጊዜ ያለፈበት ነው የሚለው አመለካከት የተዛባ በመሆኑ እንዲህ ዓይነቱ ጠባብ አስተሳሰብ ተጽዕኖ እንዲያደርግብን መፍቀድ አይገባንም!
ይሁን እንጂ እንደ አንተ ዓይነት ፆታ ላለው ሰው የፍቅር ስሜት ቢያድርብህስ? ግብረ ሰዶማዊ ነህ ማለት ነው? በፍጹም። ‘በአፍላ የጉርምስና ዕድሜ’ ላይ እንደመሆንህ መጠን አንተ ባትፈልገውም የፆታ ስሜትህ ሊቀሰቀስ እንደሚችል አስታውስ። (1 ቆሮንቶስ 7:36) አንዳንድ ጊዜ ከአንተ ጋር ተመሳሳይ ፆታ ላለው ሰው የፍቅር ስሜት ቢያድርብህ እንዲህ ዓይነቱ ስሜት ግብረ ሰዶማዊ መሆንህን የሚያመለክት እንደሆነ ሊሰማህ አይገባም። ብዙውን ጊዜ ይህ ዓይነቱ ዝንባሌ በጊዜ ሂደት ይጠፋል። እስከዚያው ድረስ ግን ግብረ ሰዶም ከመፈጸም መራቅ ይኖርብሃል። ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
መዝሙር 139:23, 24) ይሖዋ “ከማሰብ ችሎታ ሁሉ በላይ” የሆነውን ሰላም በመስጠት ሊያጠነክርህ ይችላል። ይህ ሰላም ‘ልብህንና አእምሮህን ይጠብቅልሃል’ እንዲሁም መጥፎ ምኞቶች ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶችን ወደ መፈጸም እንዳይመሩህ የሚረዳህን “ከሰብዓዊ ኃይል በላይ [የሆነ] ኃይል” ይሰጥሃል።—ፊልጵስዩስ 4:6, 7፤ 2 ቆሮንቶስ 4:7
ስለ ጉዳዩ ጸልይ። ዳዊት እንዳደረገው ይሖዋን እንዲህ በማለት ለምነው፦ “መርምረኝ፤ ልቤንም ዕወቅ፤ ፈትነኝ፤ ሐሳቤንም ዕወቅ፤ የክፋት መንገድ በውስጤ ቢኖር እይ፤ በዘላለምም መንገድ ምራኝ።” (አእምሮህን በሚያንጹ ነገሮች ሙላው። (ፊልጵስዩስ 4:8) መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ አንብብ። የአምላክ ቃል፣ በአእምሮህም ሆነ በልብህ ላይ የሚያሳድረውን በጎ ተጽዕኖ ፈጽሞ አቅልለህ አትመልከተው። (ዕብራውያን 4:12) ጄሰን የተባለ አንድ ወጣት እንዲህ ይላል፦ “በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት እንደ 1 ቆሮንቶስ 6:9, 10 እና ኤፌሶን 5:3 ያሉ ጥቅሶች በጣም ረድተውኛል። መጥፎ ምኞት ሲያድርብኝ እነዚህን ጥቅሶች አነባለሁ።”
ከብልግና ምስሎችና ጽሑፎች እንዲሁም ግብረ ሰዶምን ከሚያበረታቱ ፕሮፖጋንዳዎች ራቅ። (ቆላስይስ 3:5) መጥፎ ምኞቶች በውስጥህ እንዲቀሰቀሱ ከሚያደርግ ከማንኛውም ነገር ራቅ። ይህም የብልግና ምስሎችንና ጽሑፎችን እንዲሁም አንዳንድ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችንና ፊልሞችን ይጨምራል፤ ሌላው ቀርቶ የፆታ ስሜት የሚቀሰቅስ አለባበስ ያላቸውን ሞዴሎች የሚያሳዩ የፋሽን መጽሔቶችን ወይም ሰውነትን የሚያጋልጥ አለባበስ ያላቸውን ሰዎች የሚያሳዩ ጡንቻን ለማፈርጠም የሚረዱ መጽሔቶችን ከመመልከት መራቅ ይኖርብሃል። የረከሱ ሐሳቦች ወደ አእምሮህ ሲመጡ ንጹሕ በሆኑ ሐሳቦች ለመተካት ጥረት አድርግ። በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኝ አንድ ወጣት “ከግብረ ሰዶም ጋር የተያያዙ ምኞቶች በውስጤ ሲቀሰቀሱ ቶሎ ብዬ በምወደው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ላይ ማሰላሰል እጀምራለሁ” ብሏል።
እርግጥ ነው፣ አንዳንዶች እንዲህ ዓይነቱን ስሜት ለማስወገድ ብዙ መድከም እንደማያስፈልግ፣ ከዚህ ይልቅ ‘የፆታ ስሜትህን ማስተናገድ’ እንዲሁም ‘ማንነትህን መቀበል’ እንዳለብህ ይናገሩ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን በውስጥህ የሚቀሰቀሱትን መጥፎ ዝንባሌዎች ማሸነፍ እንደምትችል ይናገራል! ለምሳሌ፣ አንዳንድ የጥንት ክርስቲያኖች ቀድሞ ግብረ ሰዶማውያን የነበሩ ቢሆንም እንደተለወጡ ይነግረናል። (1 ቆሮንቶስ 6:9-11) እነዚህ ሰዎች እንኳ አኗኗራቸውን መለወጥ ከቻሉ አንተም በልብህ ውስጥ ያለውን እንዲህ ዓይነት ስሜት ማሸነፍ ትችላለህ።
ይሁንና እንዲህ ዓይነቱን ስሜት ማስወገድ ቢያስቸግርህስ? ለዚህ ስሜት አትሸነፍ! ይሖዋ ግብረ ሰዶም መፈጸምን ያወግዛል። ስለዚህ አንድ ሰው እንደ ራሱ ዓይነት ፆታ ላለው ሰው የሚሰማውን የፍቅር ስሜት ለማሸነፍ የሚታገል ቢሆንም ማድረግ የሚችለው አንድ ነገር አለ፦ እንዲህ ባለው ስሜት ተገፋፍቶ ግብረ ሰዶም ላለመፈጸም መምረጥ ይችላል።
ነገሩን በምሳሌ ለማስረዳት ያህል፣ አንድ ሰው “ግልፍተኛ” ነበር እንበል። (ምሳሌ 29:22) ይህ ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ከማጥናቱ በፊት ቁጣውን ለመቆጣጠር አይሞክር ይሆናል። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስን ካጠና በኋላ ራስን መግዛት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ መገንዘብ ይጀምራል። ይህ ሲባል ግን ከዚያ በኋላ ፈጽሞ አይናደድም ማለት ነው? አይደለም። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ በቁጣ መገንፈልን በተመለከተ ምን እንደሚል ስለሚያውቅ ስሜቱ እንዲያሸንፈው አይፈቅድም።
እንደ ራሱ ዓይነት ፆታ ላላቸው ሰዎች የፍቅር ስሜት የሚሰማውን ግለሰብ በተመለከተም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው፤ ይህ ሰው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ግብረ ሰዶም ያለውን አመለካከት ከተማረ በኋላም አንዳንድ ጊዜ ተገቢ ያልሆነ ስሜት ሊሰማው ይችላል። ሆኖም ግብረ ሰዶምን በተመለከተ የይሖዋ ዓይነት አመለካከት ማዳበሩ ይህንን ምኞቱን ለመቆጣጠር ኃይል ሊሰጠው ይችላል።
ተስፋ አትቁረጥ!
እንደ አንተ ዓይነት ፆታ ላላቸው ሰዎች ከሚሰማህ የፍቅር ስሜት ጋር የምትታገል ከሆነ እንደሚከተለው ብሎ እንደተናገረው ወጣት ይሰማህ ይሆናል፦ “የሚሰማኝን ስሜት ለመለወጥ ጥረት አደርጋለሁ። ይሖዋ እንዲረዳኝ እጸልያለሁ። መጽሐፍ ቅዱስን አነባለሁ። ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዙ ንግግሮችን አዳምጣለሁ። ከዚህ ሌላ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገብቶኛል።”
አንተም እንደዚህ የሚሰማህ ከሆነ ከባድ ትግል ውስጥ ገብተሃል ማለት ነው። ይህንን ሁኔታ ለማሸነፍ አቋራጭ መንገድ የለውም። ይሁንና አምላክን ለማስደሰት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው፣ እሱ ካወጣቸው የሥነ ምግባር መሥፈርቶች ጋር ተስማምቶ መኖርና ከሥነ ምግባር ብልግና መራቅ ይኖርበታል፤ ምንም ያህል ከባድ ቢሆንበትም ይህን እንዲያደርግ ይጠበቅበታል። አምላክ ከልብህ ጋር * (1 ዮሐንስ 3:19, 20) የአምላክን ትእዛዛት መፈጸምህ የእሱን በረከት ለማግኘት በር ይከፍትልሃል። የአምላክን ሕግ መጠበቅ ትልቅ “ወሮታ አለው።” (መዝሙር 19:11) አሁንም እንኳ በዚህ በመከራ በተሞላ ዓለም ውስጥ ከሁሉ የተሻለ ሕይወት መምራት ትችላለህ።
የምታደርገውን ትግል እንደሚመለከትና እሱን ለማገልገል ለሚጥሩ ሰዎች እንደሚያዝን ፈጽሞ አትዘንጋ።እንግዲያው በአምላክ በመታመን መጥፎ ምኞቶችን ለማስወገድ ትግል ማድረግህን ቀጥል። (ገላትያ 6:9) ‘ክፉ የሆነውን ነገር ለመጸየፍና ጥሩ የሆነውን ነገር አጥብቀህ ለመያዝ’ ጥረት አድርግ። (ሮም 12:9) ጥረት ማድረግህን ከቀጠልክ በውስጥህ የሚሰሙህ መጥፎ ምኞቶች ጊዜ እያለፈ ሲሄድ እየከሰሙ መምጣታቸው አይቀርም። ከሁሉ በላይ ደግሞ፣ ከግብረ ሰዶም ጋር የተያያዙ ድርጊቶችን ከመፈጸም መራቅህ አምላክ ባዘጋጀው ጽድቅ የሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ ለዘላለም የመኖር ተስፋ እንዲኖርህ ያደርጋል።
ለተቃራኒ ፆታ የሚሰማህን የፍቅር ስሜት መቆጣጠር የምትችለው እንዴት ነው?
[የግርጌ ማስታወሻ]
^ አን.21 የፆታ ብልግና የፈጸመ ክርስቲያን የጉባኤ ሽማግሌዎችን እርዳታ መጠየቅ ይኖርበታል።—ያዕቆብ 5:14, 15
ቁልፍ ጥቅስ]
“ፈትነኝ፤ ሐሳቤንም ዕወቅ፤ የክፋት መንገድ በውስጤ ቢኖር እይ።”—መዝሙር 139:23, 24
ጠቃሚ ምክር
ወንድነት ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ትክክለኛ አመለካከት ለማዳበር ኢየሱስ የተወውን ምሳሌ ማጥናቱ ጠቃሚ ነው። (1 ጴጥሮስ 2:21) ኢየሱስ የወንድነት ባሕርይን ከደግነት ጋር አጣምሮ በማንጸባረቅ ረገድ ግሩም አርዓያ ነው።
ይህን ታውቅ ነበር?
ምኞቶችህን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ባትችልም እንኳ የምትወስደውን እርምጃ መቆጣጠር ትችላለህ። መጥፎ ምኞቶች ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶችን ወደ መፈጸም እንዳይመሩህ ማድረግ አለማድረግ የአንተ ምርጫ ነው።
ላደርጋቸው ያሰብኳቸው ነገሮች
አንድ ሰው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ግብረ ሰዶምን የሚያወግዘው ለምን እንደሆነ ቢጠይቀኝ እንዲህ እለዋለሁ፦ ․․․․․
አንድ ሰው፣ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ሐሳብ ድርቅ ያለ ነው ቢለኝ እንዲህ በማለት አስረዳዋለሁ፦ ․․․․․
ከዚህ ርዕሰ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ወላጆቼን ልጠይቃቸው የምፈልገው ነገር ․․․․․
ምን ይመስልሃል?
● አምላክ ግብረ ሰዶምን የሚያወግዘው ለምንድን ነው?
● ከግብረ ሰዶም ለመራቅ የትኞቹን እርምጃዎች መውሰድ ትችላለህ?
● አምላክ ስለ ግብረ ሰዶም ያለውን አመለካከት መቀበል ሲባል ግብረ ሰዶማውያንን መጥላት ማለት ነው?
[በገጽ 236 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]
በዓለም ላይ የሚታየው የተዛባ አመለካከት ያሳደረብኝ ተጽዕኖ በውስጤ ከሚሰማኝ የፆታ ስሜት ጋር በተያያዘ የተፈጠረብኝን ግራ መጋባት ይበልጥ አባባሰው። አሁን ግን ግብረ ሰዶምን ከሚያበረታታ ማንኛውም ነገር ወይም ግለሰብ እርቃለሁ።”—አና
[በገጽ 233 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ሁሉም ወጣቶች በፊታቸው ሁለት ምርጫ ተቀምጦላቸዋል፦ ፆታን በተመለከተ በዓለም ላይ የሚታየውን ያዘቀጠ አመለካከት መቀበል አሊያም በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘውን ላቅ ያለ የሥነ ምግባር ጎዳና መከተል