ከታላቁ አስተማሪ ተማር

ከሁሉ የተሻለ መመሪያ የሚገኘው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው። ልጆች አንዳንድ ሰዎች የሚሏቸውን ሳይሆን በሰማይ ያለው አባታቸው የሚነግራቸውን መማር ይችላሉ።

ወላጆች ለልጆቻቸው ሊያደርጓቸው የሚገቡ ነገሮች

ይህ መጽሐፍ የተዘጋጀው ልጆችና መጽሐፉን የሚያነቡላቸው ሰዎች፣ አስፈላጊ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጠቃሚ ውይይት እንዲያደርጉ ለማበረታታት ታስቦ ነው።

ምዕራፍ 1

ኢየሱስ ታላቅ አስተማሪ የነበረው ለምንድን ነው?

ኢየሱስ ስለ የትኞቹ ነገሮች አስተምሯል? ያስተማረውን ነገር ያገኘው ከየት ነው?

ምዕራፍ 2

ከሚወደን አምላክ የተላከ ደብዳቤ

እሱ የላከው ደብዳቤ ከየትኛውም መጽሐፍ ይበልጥ ውድ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ ይገኛል።

ምዕራፍ 3

ሁሉንም ነገሮች የሠራው ፈጣሪ

ወፎችን የፈጠረውና መዘመር ያስተማራቸው ማን ነው? ሣርን የፈጠረው ማን ነው? አንተንስ የፈጠረህ ማን ነው?

ምዕራፍ 4

አምላክ ስም አለው

ሁላችንም ስም አለን። የአምላክ ስም ማን እንደሆነ ታውቃለህ? ስሙን ማወቅ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 5

“ልጄ ይህ ነው”

ኢየሱስ ከሌሎች የተለየ ሰው እንዲሆን ያደረገው ምንድን ነው?

ምዕራፍ 6

ታላቁ አስተማሪ ሌሎች ሰዎችን አገልግሏል

አንድ ሰው ጥሩ ነገር ሲያደርግልህ ደስ አይልህም? ሁላችንም ጥሩ ነገር ሲደረግልን ደስ ይለናል፤ ታላቁ አስተማሪም ይህን ያውቅ ነበር።

ምዕራፍ 7

ታዛዥነት ይጠብቅሃል

ልጆች ከአዋቂዎች መማር ይችላሉ። አምላክ እንድናደርግ የሚያዘን ነገር ምንጊዜም ትክክል ነው።

ምዕራፍ 8

ከእኛ በላይ የሆኑ አሉ

አንዳንዶቹ ጥሩዎች ሌሎቹ ግን መጥፎዎች ናቸው።

ምዕራፍ 9

የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች መቋቋም ያስፈልገናል

አንድ ሰው ትክክል ያልሆነ ነገር እንድታደርግ ቢነግርህ ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

ምዕራፍ 10

ኢየሱስ ከአጋንንት የበለጠ ኃይል አለው

አጋንንትን የምንፈራበት ምክንያት የለም፤ ሆኖም እንዳያታልሉን መጠንቀቅ ያስፈልገናል።

ምዕራፍ 11

ከአምላክ መላእክት የሚገኝ እርዳታ

የአምላክ መላእክት ይሖዋን የሚወዱና እሱን የሚያገለግሉ ሰዎችን ይረዳሉ።

ምዕራፍ 12

ኢየሱስ እንድንጸልይ አስተምሮናል

ቀንም ሆነ ማታ በማንኛውም ሰዓት አምላክን ብታነጋግረው ይሰማሃል።

ምዕራፍ 13

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት

ምን ዓይነት ሰዎች ነበሩ?

ምዕራፍ 14

ይቅር ማለት ያለብን ለምንድን ነው?

ኢየሱስ ነጥቡ ግልጽ እንዲሆንልን ሲል አንድ ታሪክ ተናገረ።

ምዕራፍ 15

ደግ ስለመሆን የተሰጠ ትምህርት

ከደጉ ሳምራዊ ታሪክ ትምህርት ውሰድ።

ምዕራፍ 16

ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው ነገር ምንድን ነው?

በአምላክ ዘንድ ሀብታም መሆን የምንችለው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 17

ደስተኛ መሆን የሚቻልበት መንገድ

ታላቁ አስተማሪ አንድ ትልቅ ሚስጥር ተናገረ።

ምዕራፍ 18

ለተደረገልህ ነገር አስታውሰህ ታመሰግናለህ?

ከአሥሩ የሥጋ ደዌ በሽተኞች ትምህርት መውሰድ ትችላለህ።

ምዕራፍ 19

መጣላት ተገቢ ነው?

ሰዎች ሲጣሉ ብታይ ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

ምዕራፍ 20

ሁልጊዜ ቅድሚያ ማግኘት ትፈልጋለህ?

ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ ጉዳይ ሲጨቃጨቁ ኢየሱስ ምን አላቸው?

ምዕራፍ 21

ጉራ መንዛት ይኖርብናል?

ኢየሱስ ስለ አንድ ፈሪሳዊና ስለ አንድ ቀረጥ ሰብሳቢ የሚገልጽ ታሪክ ተናገረ።

ምዕራፍ 22

መዋሸት የሌለብን ለምንድን ነው?

ይሖዋ ሐናንያን እና ሰጲራን ምን እንዳደረጋቸው አንብብ።

ምዕራፍ 23

ሰዎች የሚታመሙት ለምንድን ነው?

ሰዎች ጨርሶ የማይታመሙበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

ምዕራፍ 24

ሌባ እንዳትሆን ተጠንቀቅ!

የራሳቸው ያልሆነን ነገር የወሰዱ አራት ሰዎችን ታሪክ አንብብ።

ምዕራፍ 25

መጥፎ ነገር የሚሠሩ ሰዎች ሊለወጡ ይችላሉ?

የሳኦል እና የአንዲት አመንዝራ ሴት ምሳሌ መልሱን ይሰጠናል።

ምዕራፍ 26

ጥሩ ነገር መሥራት ከባድ የሆነው ለምንድን ነው?

መጥፎ ሰዎች፣ እነሱ ያሉህን ካላደረግህ ምን ይሰማቸዋል?

ምዕራፍ 27

አምላክህ ማን ነው?

ሰዎች በርካታ አማልክትን ያመልካሉ። አንተ ምን ማድረግ ይኖርብሃል? ሦስት ዕብራውያን ወጣቶች መልሱን ይሰጡናል።

ምዕራፍ 28

ማንን መታዘዝ እንዳለብን ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?

“የቄሳር የሆነውን ነገር ለቄሳር የአምላክ የሆነውን ነገር ደግሞ ለአምላክ መልሳችሁ ስጡ።”

ምዕራፍ 29

ሁሉም ዓይነት ግብዣ አምላክን ያስደስተዋል?

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ የተለያዩ ግብዣዎች እንዳሉ ታውቃለህ? አምላክ ስለ እነዚህ ግብዣዎች ምን እንደተሰማው ማወቅ እንችላለን።

ምዕራፍ 30

ያለብንን ፍርሃት ለማሸነፍ የሚያስችል እርዳታ

ታላቁ አስተማሪ፣ ይሖዋን ማገልገል ቀላል እንደሚሆን አልተናገረም። ሆኖም ድፍረትና እርዳታ ማግኘት የሚቻልበት መንገድ አለ።

ምዕራፍ 31

መጽናኛ ማግኘት የሚቻለው ከየት ነው?

የሐዘንና የብቸኝነት ስሜት ቢሰማህ ምን ማድረግ ትችላለህ?

ምዕራፍ 32

ኢየሱስ ጥበቃ ያገኘው እንዴት ነው?

ኢየሱስ ልጅ እያለ ሊገድሉት ከሞከሩት ሰዎች ይሖዋ እንዴት እንደጠበቀው አንብብ።

ምዕራፍ 33

ኢየሱስ ሊጠብቀን ይችላል

ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት የሚወዱትን ሰዎች እንዴት እንደሚጠብቃቸው አሳይቷል።

ምዕራፍ 34

ስንሞት ምን እንሆናለን?

ሞትን ወይም የሞቱ ሰዎችን ልትፈራ ይገባል?

ምዕራፍ 35

ከሞት ልንነሳ እንችላለን!

አምላክ፣ ልጆችን ጨምሮ የሞቱ ሰዎችን ከሞት እንዲያስነሳ ለኢየሱስ ኃይል ሰጥቶታል።

ምዕራፍ 36

ከሞት የሚነሱት እነማን ናቸው? የሚኖሩትስ የት ነው?

ኢየሱስ ለእነዚህ ጥያቄዎች ምን መልስ ሰጥቷል?

ምዕራፍ 37

ይሖዋንና ልጁን ማስታወስ

ይሖዋና ኢየሱስ ያደረጉልንን ነገር ለማስታወስ የሚረዳን አንድ ልዩ መንገድ ኢየሱስ ለተከታዮቹ አሳይቷቸዋል።

ምዕራፍ 38

ኢየሱስን መውደድ ያለብን ለምንድን ነው?

የዘላለም ሕይወት እንድናገኝ ሲል ፍጹም ሕይወቱን ሰጠ!

ምዕራፍ 39

አምላክ ልጁን አልረሳውም

ኢየሱስ ከሞት ተነሣ።

ምዕራፍ 40

አምላክን ማስደሰት የምንችለው እንዴት ነው?

አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌ “ልጄ ሆይ፤ ጠቢብ ሁን፤ ልቤን ደስ አሰኘው” ይላል።

ምዕራፍ 41

አምላክን የሚያስደስቱ ልጆች

አምላክን ለማስደሰት ምን ማድረግ ትችላለህ?

ምዕራፍ 42

ሥራ መሥራት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?

ሥራ ለአእምሯችንም ሆነ ለአካላችን ጠቃሚ ነው። በሥራ መደሰት የምትችለው እንዴት እንደሆነ አንብብ።

ምዕራፍ 43

ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እነማን ናቸው?

ወላጆቻችን አንድ ባይሆኑም፣ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎች አሉ?

ምዕራፍ 44

ጓደኞቻችን አምላክን የሚወዱ መሆን ይኖርባቸዋል

“አትሳቱ፤ ‘መጥፎ ጓደኝነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።’”

ምዕራፍ 45

የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? እንደምንፈልገው የምናሳየውስ እንዴት ነው?

ኢየሱስ መላዋን ምድር በሚገዛበት ወቅት ትልቅ ለውጥ ያመጣል።

ምዕራፍ 46

ዓለም በውኃ ጠፋ—ዳግመኛ በውኃ ይጠፋ ይሆን?

ጻድቃን በምድር ላይ ለዘላለም ይኖራሉ።

ምዕራፍ 47

አርማጌዶን እንደቀረበ ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?

ምልክቱ በግልጽ እየታየ ነው።

ምዕራፍ 48

አምላክ በሚያመጣው ሰላማዊ አዲስ ዓለም ውስጥ መኖር ትችላለህ

በዚያ ለዘላለም ለመኖር ምን ማድረግ ያስፈልግሃል?