በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ


እዚህ ጽሑፍ ላይ ካለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተሟላ ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

እዚህ ጽሑፍ ላይ ካለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተሟላ ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

የሚያስተምርህ ሰው ያስፈልግሃል፦ ይህን ጽሑፍ የሰጠህን ሰው መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያስተምርህ ጠይቀው፤ ወይም jw.org በተባለው ድረ ገጻችን ላይ ለዚህ ዓላማ የተዘጋጀውን ቅጽ ሙላ።

የመጀመሪያው ክፍል

እያንዳንዱን አንቀጽና በደማቅ የተጻፉትን ጥያቄዎች (ሀ) እንዲሁም ዋና ዋና ነጥቦቹን የሚያጎሉትን ጥቅሶች (ለ) አንብብ። ከአንዳንዶቹ ጥቅሶች አጠገብ “አንብብ” የሚል መመሪያ እንደሚገኝ ልብ በል።

ሁለተኛው ክፍል

ጠለቅ ያለ ጥናት በሚለው ሥር ያለው አጠር ያለ መግለጫ (ሐ) ቀጥሎ የሚብራራውን ሐሳብ ይገልጻል። ንዑስ ርዕሶቹ (መ) ዋና ዋና ነጥቦቹን ይዘዋል። ጥቅሶቹን አንብብ፤ የጥያቄዎቹን መልስ ለማግኘት ሞክር፤ እንዲሁም ቪዲዮዎቹን (ሠ) ተመልከት።

ሥዕሎቹንና የሥዕሎቹን መግለጫዎች (ረ) ትኩረት ሰጥተህ ተመልከትበተጨማሪም አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ (ሰ) በሚለው ሥር የቀረቡትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር

የመጨረሻው ክፍል

ማጠቃለያ እና ክለሳ (ሸ) የሚሉት ክፍሎች የምዕራፉን ሐሳብ ጠቅለል አድርገው ይገልጻሉ። ምዕራፉን አጥንተህ የጨረስክበትን ቀን ጻፍ። ግብ (ቀ) የሚለው ክፍል በሥራ ላይ ልታውል የምትችላቸውን አንዳንድ ነጥቦች ይጠቁምሃል። ምርምር አድርግ (በ) የሚለው ክፍል ደግሞ ልታነብ ወይም ልትመለከት የምትችላቸውን ተጨማሪ ርዕሶች ወይም ቪዲዮዎች ይዟል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማውጣት የምትችለው እንዴት ነው?

ጥቅሶች በሚጠቀሱበት ጊዜ መጀመሪያ የመጽሐፉ ስም (ሀ)፣ ቀጥሎ ምዕራፉ (ለ) ከዚያ በኋላ ደግሞ ቁጥሩ ወይም ቁጥሮቹ (ሐ) ይጻፋሉ። ለምሳሌ ያህል፣ ዮሐንስ 17:3 ሲባል ዮሐንስ ምዕራፍ 17 ቁጥር 3 ማለት ነው።