ኢንተርኔት ባይኖርም ልታነባቸውና ልታያቸው የምትችል በመቶዎች የሚቆጠሩ መጻሕፍት፣ ብሮሹሮች፣ ትራክቶችና ቪዲዮዎች JW Library ላይ አሉ።

ጽሑፎችን ለማውረድና ለመጠቀም እነዚህን መመሪያዎች ተከተል፦

 የሕትመት ውጤቶችን ማውረድ

JW Library ላይ፣ ኢንተርኔት ባይኖርም ልታነባቸውና ልታያቸው የምትችል በርካታ የሕትመት ውጤቶችን ማውረድ ትችላለህ።

  • ዋናውን ማውጫ ከፍተህ የሕትመት ውጤቶች የሚለውን ስትጫን የሕትመት ውጤቶቹን ዝርዝር ታገኛለህ።

  • ቋንቋዎች የሚለውን ስትጫን የሕትመት ውጤቶች የሚገኙባቸውን የተለያዩ ቋንቋዎች ዝርዝር ታገኛለህ። ከዚያም የምትፈልገውን ቋንቋ ምረጥ። ብዙ ጊዜ የተጠቀምክባቸው ቋንቋዎች ከላይ ይሆናሉ። የምትፈልገውን ቋንቋ ስም በመጻፍም ቋንቋውን መፈለግ ትችላለህ።

JW Library ላይ የሕትመት ውጤቶችን ማግኘት የምትችልባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ።

በዓይነት የሚለው ክፍል በመረጥከው ቋንቋ የሚገኙትን የሕትመት ውጤቶች በየዓይነታቸው ይኸውም መጻሕፍት፣ ትራክት ወይም ቪዲዮዎች በማለት ከፋፍሎ ያስቀምጥልሃል። አንዳንዶቹን ምድቦች ስትጫን በሥራቸው ያሉ ዝርዝሮች ይታያሉ፤ ለምሳሌ መጠበቂያ ግንብ በዓመት፣ ቪዲዮዎች ደግሞ በርዕሰ ጉዳይ ተከፋፍለው ይታያሉ። ሁሉንም ዝርዝሮች ለማየት ዋናው ዝርዝር የሚለውን ተጫን።

አዲስ ነገር በሚለው ሥር በመረጥከው ቋንቋ አዲስ የወጡ የሕትመት ውጤቶችን ታገኛለህ።

የደመና ምልክት ያለባቸው ገና ያላወረድካቸው የሕትመት ውጤቶች ናቸው። የሕትመት ውጤቱን ለማውረድ ጽሑፉን ተጫን። ጽሑፉን ስታወርድ የደመናው ምልክት ይጠፋል። ለማንበብ ደግሞ ያወረድከውን ጽሑፍ ተጫን።

ያወረድኳቸው በሚለው ሥር በየትኛውም ቋንቋዎች ያወረድካቸውን ጽሑፎች በሙሉ መመልከት ትችላለህ። እነዚህ ጽሑፎች ብዙ ጊዜ የተከፈቱ፣ ብዙ ጊዜ ያልተከፈቱ፣ ወይም ትልቅ መጠን በሚል ቅደም ተከተላቸውን ማስተካከል ትችላለህ።

የሕትመት ውጤቶችን ማጥፋት

 አንድን ጽሑፍ ካልፈለግከው ወይም ተጨማሪ ማስቀመጫ ቦታ ማግኘት ከፈለክ ልታጠፋው ትችላለህ።

ዋናውን ማውጫ ክፈትና የሕትመት ውጤቶች የሚለውን ስትጫን የጽሑፎቹን ዝርዝር (ለምሳሌ፣ መጻሕፍት የሚል) ታገኛለህ። ማጥፋት በምትፈልገው የሕትመት ውጤት ላይ ያለውን ሌሎች የሚለውን ተጫን፤ ከዚያም አጥፋ የሚለውን ተጫን።

ተጨማሪ ማስቀመጫ ቦታ ለማግኘት ብዙ ጊዜ ያልተከፈቱትን ወይም ትልቅ መጠን ያላቸውን ማጥፋት ትችላለህ። ዋናውን ማውጫ በመክፈት የሕትመት ውጤቶች የሚለውን ተጫን። ከዚያም ያወረድኳቸው የሚለው ክፈት፤ ከዚያም ብዙ ጊዜ ያልተከፈቱ ወይም ትልቅ መጠን በማለት መለየት ትችላለህ። ከዚያም የማትፈልገው ጽሑፍ አጥፋ።

የሕትመት ውጤቶችን ማደስ

 አንዳንድ ጊዜ ያወረድካቸው ጽሑፎች መታደስ ያስፈልጋቸው ይሆናል።

መታደስ የሚያስፈልጋቸው ጽሑፎች ላይ አነቃቃ የሚል ምልክት ይታያል። ጽሑፉን ስትጫን ጽሑፉ መታደስ እንደሚያስፈልገው የሚጠቁም መልእክት ይታያል። ጽሑፉን ለማደስ አውርድ የሚለውን ተጫን፤ ያልታደሰውን ጽሑፍ ማንበብ ከፈለግክ ግን በኋላ የሚለውን ተጫን።

ያወረድካቸው የሕትመት ውጤቶች መታደስ ያስፈልጋቸው እንደሆነ ለማየት ዋናውን ማውጫ ክፈት፤ ከዚያም የሕትመት ውጤቶች የሚለውን ተጫን። መታደስ የሚያስፈልገው ነገር ካለ ለመታደስ የተዘጋጁ የሚል ክፍል ይታያል። ለመታደስ ዝግጁ የሆኑ ጽሑፎች ዝርዝር በሙሉ የሚታዩት በዚህ ክፍል ውስጥ ነው። አንድን ጽሑፍ ብቻ ለማደስ ከፈለግክ ጽሑፉን ተጫን፤ ሁሉንም ለማደስ ከፈለግክ ደግሞ ሁሉንም አድስ የሚለውን ተጫን።

እነዚህ ገጽታዎች የወጡት የካቲት 2015 JW Library 1.4 ሲወጣ ነው፤ አንድሮይድ 2.3 ወይም ከዚያ በላይ ለሚጠቀሙ ይሠራል። እነዚህን ገጽታዎች ማግኘት ካልቻልክ “JW Libraryን መጠቀም ጀምር—አንድሮይድ” የሚለውን ከፍተህ አዳዲስ ገጽታዎች በሚለው ርዕስ ሥር ያሉትን መመሪያዎች ተከተል።