በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

JW LIBRARY

መጽሐፍ ቅዱሶችን ማውረድና መጠቀም—አንድሮይድ

መጽሐፍ ቅዱሶችን ማውረድና መጠቀም—አንድሮይድ

JW Library በዋነኛነት የተዘጋጀው መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብና ለማጥናት እንዲረዳ ነው።

መጽሐፍ ቅዱሶችን ለማውረድና ለመጠቀም እነዚህን መመሪያዎች ተከተል፦

 መጽሐፍ ቅዱስ ማውረድ

የተለያዩ ትርጉሞችን በማውረድ ኢንተርኔት ሳይኖርም ማንበብና ማጥናት ትችላለህ።

  • ዋናውን ማውጫ በመክፈት መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ስትጫን የመጻሕፍቱን ዝርዝር ታገኛለህ።

  • ቋንቋዎች የሚለውን በመጫን የተለያዩ ትርጉሞችን ማግኘት ትችላለህ። ብዙ ጊዜ የምትጠቀምባቸው ቋንቋዎች በዝርዝሩ ውስጥ ከላይ ይገኛሉ። የቋንቋውን ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሙን ስም በመጻፍም መፈለግ ትችላለህ። ለምሳሌ “i n t” በመጻፍ በእንግሊዝኛ የሚገኘውን ኪንግደም ኢንተርሊኒየር ወይም “p o r t” በመጻፍ በፖርቱጋልኛ የሚገኙ መጽሐፍ ቅዱሶችን በሙሉ ማግኘት ትችላለህ።

  • ያላወረድካቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች የደመና ምልክት ይታይባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱሱን ለማውረድ የደመናውን ምልክት ተጫን። መጽሐፍ ቅዱሱን ስታወርደው የደመናው ምልክት ይጠፋል። ያወረድከውን መጽሐፍ ቅዱስ ለማንበብ ቋንቋውን ተጫን።

የምትፈልገውን መጽሐፍ ቅዱስ በዝርዝሩ ውስጥ ካላገኘህ ትንሽ ቆይተህ ሞክር። አዳዲስ ትርጉሞች ሲወጡ በዝርዝሩ ውስጥ ይካተታሉ።

 ያወረድከውን መጽሐፍ ቅዱስ ማጥፋት

አንድን መጽሐፍ ቅዱስ ካልፈለግከው ወይም ተጨማሪ ማስቀመጫ ቦታ ለማግኘት ልታጠፋው ትችላለህ።

ዋናውን ማውጫ በመክፈት መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ተጫን፤ ከዚያም ቋንቋዎች የሚለውን ቁልፍ ስትጫን የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን ታገኛለህ። ማጥፋት በምትፈልገው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን ሌሎች የሚለውን ተጫን፤ ከዚያም አጥፋ የሚለውን ተጫን።

 መጽሐፍ ቅዱሱን ማደስ

አንዳንድ ጊዜ ያወረድካቸው መጽሐፍ ቅዱሶች መታደስ ያስፈልጋቸው ይሆናል።

መታደስ በሚያስፈልጋቸው መጽሐፍ ቅዱሶች ላይ አነቃቃ የሚል ምልክት ይታያል። መጽሐፍ ቅዱሱን ስትጫን መታደስ እንደሚያስፈልገው የሚጠቁም መልእክት ይታያል። ለማደስ ከፈለግክ አውርድ የሚለውን ተጫን፤ ያልታደሰውን ለማንበብ ከፈልግክ ግን በኋላ የሚለውን ተጫን።

እነዚህ ገጽታዎች የወጡት የካቲት 2015 JW Library 1.4 ሲወጣ ነው፤ አንድሮይድ 2.3 ወይም ከዚያ በላይ ለሚጠቀሙ ይሠራል። እነዚህን ገጽታዎች ማግኘት ካልቻልክ “JW Libraryን መጠቀም ጀምር—አንድሮይድ” የሚለውን ከፍተህ አዳዲስ ገጽታዎች በሚለው ርዕስ ሥር ያሉትን መመሪያዎች ተከተል።