በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

JW LIBRARY SIGN LANGUAGE

JW Library Sign Language ያሉት ገጽታዎች

JW Library Sign Language ያሉት ገጽታዎች

የምልክት ቋንቋ JW Library የይሖዋ ምሥክሮች ያዘጋጁት ሕጋዊ አፕሊኬሽን ነው። ይህ አፕሊኬሽን በjw.org ላይ የሚወጡ በምልክት ቋንቋ የተዘጋጁ ቪዲዮዎችን ለማውረድ፣ በተደራጀ መልኩ ለማስቀመጥና ለማጫወት ያስችላል።

መጽሐፍ ቅዱስንም ሆነ በምልክት ቋንቋ የተዘጋጁ ሌሎች ጽሑፎችን በቪድዮ ተመልከት። ያለ ኢንተርኔት ማየት እንድትችል ቪዲዮዎቹን በማውረድ እንደ ሞባይል ባሉ ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎች ላይ አስቀምጣቸው። ምስሎቹ ማራኪ ሲሆኑ አፕልኬሽኑ የምትፈልገውን ገጽ ለማግኘትም ሆነ ለአጠቃቀም ቀላል ነው።

 

ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ

Bible የሚለው ክፍል፣ በድረ ገጹ ላይ የወጡ የአዲስ ዓለም ትርጉም የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን በተናጥል ለማየት ያስችልሃል። ከዚህም በተጨማሪ ገና በአዲስ ዓለም ትርጉም ውስጥ ተካትተው ያልወጡ ሆኖም በሌሎች ጽሑፎች ላይ የሚገኙ በምልክት ቋንቋ የተቀዱ ጥቅሶችን መመልከት ትችላለህ። Library በሚለው ክፍል ላይ ደግሞ በjw.org ላይ የወጡ ሌሎች ጽሑፎችና ፊልሞች ይገኛሉ።

 

ጥቅሶችን በቀላሉ ማየት

በቪዲዮ የተዘጋጁ ጽሑፎችን በምትመለከትበት ጊዜ Bible የሚለውን ጠቅ አድርግ። በዚህ ጊዜ ቪዲዮው መጫወቱን ለጊዜው ያቆማል፤ ይህም ጥቅሶቹን አውጥተህ ለመመልከት ያስችልሃል። ከዚያም Library ወደሚለው ገጽ በመመለስ ቀደም ሲል የከፈትከውን ቪዲዮ ማየትህን መቀጠል ትችላለህ።

ቪዲዮዎችን በቀላሉ ማውረድ

ያላወረድካቸው ቪዲዮዎች ደብዘዝ ብለው ይታያሉ። የምትፈልገውን ቪዲዮ ከjw.org ማውረድ ከፈለግክ ያንን ቪዲዮ ጠቅ አድርግ። በገጹ ላይ የሚታዩትን ሁሉንም ቪዲዮዎች ማውረድ ከፈለግክ ደግሞ Download All የሚለውን ጠቅ አድርግ። አንድን ቪዲዮ ከማጫወቻህ ላይ ማጥፋት ከፈለግክ ቪዲዮውን ለተወሰነ ጊዜ ተጭነኸው ቆይ።

 

ማስቀመጫ ቦታ

ብዙ ቦታ የሚይዝ (ከፍተኛ ጥራት አለው) ወይም አነስተኛ ቦታ የሚይዝ (ዝቅ ያለ ጥራት አለው) ቪዲዮ መርጠህ ማውረድ ትችላለህ። የምትጠቀምበት ዕቃ SD ካርድ የሚወስድ ከሆነ ደግሞ ቪዲዮዎቹን በቀጥታ ዕቃህ ላይ ወይም SD ካርዱ ላይ ልታስቀምጥ ትችላለህ።

 

ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ የቪዲዮ ማጫወቻ

የቪዲዮ ማጫወቻውን ለመቆጣጠር የሚከተሉትን ዘዴዎች መጠቀም ትችላለህ፦

  • በሁለት ጣት ነካ ማድረግ፦ ቪዲዮውን ለማጫወት ወይም ለጊዜው ለማቆም ያስችላል።

  • ወደ ግራ ማንሸራተት፦ ወደ ቀጣዩ ትዕይንት ለማለፍ ያስችላል።

  • ወደ ቀኝ ማንሸራተት፦ ወደ ቀድሞው ትዕይንት ለመመለስ ያስችላል።

  • ወደ ላይ ማንሸራተት፦ ቪዲዮው የሚጫወትበትን ፍጥነት ለመጨመር ያስችላል። (ይህ ገጽታ ለአንድሮይድ አልተዘጋጀም።)

  • ወደ ታች ማንሸራተት፦ ቪዲዮው የሚጫወትበትን ፍጥነት ለመቀነስ ይረዳል። (ይህ ገጽታ ለአንድሮይድ አልተዘጋጀም።)

  • አንዴ ነካ ማድረግ፦ የቪዲዮ መቆጣጠሪያዎቹን ለማየት ወይም ለመደበቅ ያስችላል።

በቅርብ ቀን

  •  የራስን የቪዲዮ ዝርዝር ማውጣት

  •  በቅርቡ የታዩ ቪዲዮዎች ዝርዝር

  •  ለሌሎች የምልክት ቋንቋዎች የሚሆን እገዛ

  •  ለWindows 8 የሚሆን እገዛ