በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

JW ብሮድካስቲንግ

JW ብሮድካስቲንግ

JW ብሮድካስቲንግ በየትኛውም የዕድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ሰዎች ሊመለከቱት የሚችሉና በመንፈሳዊ የሚገነቡ ፕሮግራሞች የሚቀርቡበት የኢንተርኔት ቴሌቪዥን ነው። በJW ብሮድካስቲንግ ስቱዲዮ ውስጥ የተዘጋጁ ፕሮግራሞችና ከjw.org ላይ የተወሰዱ አንዳንድ የተመረጡ ቪዲዮዎች ይቀርቡበታል። ከስርጭት ቻናሎች ውስጥ አንዱን በመምረጥ የ24 ሰዓት ስርጭት መከታተል ወይም የቪዲዮ መምረጫውን በመጠቀም የምትፈልገውን ቪዲዮ መርጠህ ማየት ትችላለህ። ኦዲዮ በሚለው ሥር ደግሞ መዝሙሮችን፣ ድራማዎችንና ድራማዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባቦችን ጨምሮ የተለያዩ በድምፅ የተዘጋጁ ነገሮችን ማዳመጥ ትችላለህ።

በኢንተርኔት የሚተላለፈውን የቴሌቪዥን ስርጭት በኮምፒውተር፣ በታብሌት ወይም በዘመናዊ ስልኮች tv.jw.org ውስጥ በመግባት መመልከት ትችላለህ። JW ብሮድካስቲንግን Amazon Fire TVንApple TVን፣ ወይም Roku digital media playerን በመጠቀም በቴሌቪዥን መመልከት ትችላለህ።